እግዚአብሔርን ጠርቼው የመለሰልኝ ጊዜ ነበር፤ አሁን እኔ የወዳጆቼ መሳቂያ ሆኛለሁ፤ ስሕተት የሌለብኝ ፍጹሙ እኔ የሰው ሁሉ መሳለቂያ ሆኛለሁ።
ኢዮብ 12:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ችግር ባልደረሰበት ሰው ዘንድ የተቸገረን ሰው ችግር ማናናቅ ቀላል ነው። ነገር ግን ሊወድቅ የሚንገዳገደውን ሰው ትገፈትሩታላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የደላቸው በመከራ ያፌዛሉ፤ እግሩ የተንሸራተተውንም ይገፈትራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተደላድሎ የተቀመጠ ሰው መከራን ይንቃል፥ እግሩን ያዳለጠውንም ለመገፍተር ተዘጋጅቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ በተወሰነው ዕድሜ በሌሎች እንዲወድቅ፥ ቤቱም በኃጥኣን እንዲፈርስ ተዘጋጅቶአል። ነገር ግን ማንም ክፉ ሆኖ ንጹሕ እንደሚሆን አይመን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተዘልሎ በሚቀመጥ ሰው አሳብ መከራ ይናቃል፥ ነገር ግን እግሩን ሊያድጠው ተዘጋጅቶአል። |
እግዚአብሔርን ጠርቼው የመለሰልኝ ጊዜ ነበር፤ አሁን እኔ የወዳጆቼ መሳቂያ ሆኛለሁ፤ ስሕተት የሌለብኝ ፍጹሙ እኔ የሰው ሁሉ መሳለቂያ ሆኛለሁ።
እናንተ በእኔ ቦታ ሆናችሁ እኔ በእናንተ ቦታ ብሆን ኖሮ በንቀት ራሴን እየነቀነቅሁ አሁን እናንተ የምትሉትን ሁሉ በእናንተ ላይ አሳምሬ መናገር በቻልኩ ነበር።
ጨለማን አምጥቶ በተራራዎች ከመሰናከላችሁ በፊት ተስፋ ያደረጋችኹትን ብርሃን ወደ ድቅድቅ ጨለማና ወደ ጥልቅ ጭጋግ ከመለወጡ በፊት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አክብሩ።
ከዚህም በኋላ ራሴን፦ እነሆ፥ ለብዙ ዓመት የሚበቃህ ብዙ ሀብት አለህ፤ እንግዲህ ዕረፍት በማድረግ ተዝናና! ብላ! ጠጣ! ደስ ይበልህ! እለዋለሁ’ አለ።