ኢዮብ 11:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምሥጢር ማወቅ ትችላለህን? ሁሉን ቻይ አምላክንስ መርምረህ ልትደርስበት ትችላለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምስጢር ልትለካ ትችላለህን? ወይስ ሁሉን ቻዩን አምላክ መርምረህ ትደርስበታለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ልትመረምር ትችላለህን? ሁሉን የሚችል አምላክን ፍጻሜ ልትመረምር ትችላለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእግዚአብሔርን ፍለጋ ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክ ወደ ፈጠረው ፍጥረት ፍጻሜ ትደርሳለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክን ፈጽመህ ልትመረምር ትችላለህን? |
እነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ከሚሠራቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፤ የምንሰማውም ሹክሹክታውን ብቻ ነው፤ የኀይሉን ነጐድጓድማ ማን ሊያስተውል ይችላል?”
እኔ የማውቀው በጣም ትንሽ ሆኖ ሳለ ብዙ የምናገረው ለምን እንደ ሆነ ጠይቀሃል። በእርግጥ እኔ ስለማላውቃቸውና እጅግ ድንቅ ስለ ሆነ ነገር ተናግሬአለሁ።
ወደ ሰማይ ወጥቶ የወረደ ማን ነው? ነፋስን በእጁ የጨበጠ፥ ውሃን በልብሱ የቋጠረ፥ የምድርን ዳርቻ ያጸና ማን ነው? የሰውዬው ስም ማነው? የልጁስ ስም ማን ይባላል? ታውቅ እንደሆን ንገረኝ፤
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ነገር ጊዜ በመወሰን ሁሉን ነገር ውብ አድርጎ ሠርቶታል፤ ዘለዓለማዊነትንም በሰው ልቡና አሳድሮአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሁሉ እስከ መጨረሻ ያውቅ ዘንድ ለሰው የተሰጠው ዕውቀት ሙሉ አይደለም።
ከቶ አታውቅምን? ከቶስ አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘለዓለም አምላክ ነው፤ ዓለምን ሁሉ የፈጠረ እርሱ ነው፤ እርሱ ከቶ አይደክምም ወይም አይታክትም፤ ሐሳቡን መርምሮ ሊደርስበት የሚቻለው የለም።
አባቴ ሁሉን ነገር ሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ ማንም የለም። እንዲሁም ከወልድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም፤ ማንም ወልድ ካልገለጠለት በቀር አብን ሊያውቅ አይችልም።
ለእኛ ግን እግዚአብሔር በመንፈሱ አማካይነት ምሥጢሩን ገልጦልናል፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ጥልቅ የሆነውን የእግዚአብሔርን ምሥጢር እንኳ ሳይቀር ሁሉን ነገር ይመረምራል።
ይህም፦ “የጌታን ሐሳብ ማን ሊያውቀው ይችላል? ሊመክረውስ የሚችል ማን ነው?” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው። እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።
እኔ ከቅዱሳን ሁሉ የማንስ ብሆንም እንኳ ወሰን የሌለውን የክርስቶስን ባለጸግነት ለአሕዛብ እንዳበሥር በእግዚአብሔር ጸጋ ይህ ዕድል ተሰጠኝ።