ኢዮብ 11:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምነው እግዚአብሔር በተናገረና ትክክለኛውን መልስ በሰጠህ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ! ከንፈሩንም በአንተ ላይ ቢከፍት! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ! በአንተም ላይ ከንፈሩን ቢከፍት! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ! በአንተም ላይ ከንፈሩን ቢከፍት! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ! በአንተም ላይ ከንፈሩን ቢከፍት! |
“ምነው የሚሰማኝ ባገኘሁ! መከላከያዬን አቀርባለሁ፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ይመልስልኝ! ምነው ከሳሼም የክሱን ዝርዝር በጽሑፍ አቅርቦልኝ ባየሁት!
እግዚአብሔር ከኢዮብ ጋር እነዚህን ነገሮች ከተነጋገረ በኋላ ቴማናዊውን ኤሊፋዝን እንዲህ አለው፦ “እናንተ ስለ እኔ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ትክክለኛውን ነገር ስላልተናገራችሁ እኔ በአንተና በሁለቱ ጓደኞችህ ላይ ተቈጥቼአለሁ።