ኢዮብ 11:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተስፋ ስላለህ አንተም በመተማመን ትኖራለህ፤ እግዚአብሔር ስለሚጠብቅህ ያለ ስጋት ዐርፈህ ትኖራለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተስፋ ስላለ ተደላድለህ ትቀመጣለህ፤ ዙሪያህን ትመለከታለህ፣ ያለ ሥጋት ታርፋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተስፋም ስላለህ ተማምነህ ትቀመጣለህ፥ በዙሪያህ ትመለከታለህ፥ በደኅንነትም ታርፋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተስፋህንም ታገኝ ዘንድ ተዘልለህ ትቀመጣለህ፤ ያለ ኀዘንና ጭንቀትም በደኅንነት ትኖራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተስፋም ስላለህ ተዘልለህ ትቀመጣለህ፥ በዙሪያህ ትመለከታለህ፥ በደኅንነትም ታርፋለህ። |
በማለዳ እየተነሡና በምሽትም እየዘገዩ ለኑሮ መድከም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች ገና ተኝተው ሳሉ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ያዘጋጅላቸዋል።
እግዚአብሔርም ለቅዱሳኑ ሊገልጥላቸው የፈቀደው ያለውን የዚህን ምሥጢር የክብር ብልጽግና በእናንተ በአሕዛብ መካከል ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ነው። ይህም ምሥጢር በተስፋ የምንጠባበቀው ክብር የሚገኝበት ክርስቶስ በእናንተ መካከል መሆኑ ነው።