ኢዮብ 11:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሆኖም፥ ልብህን የቀና ብታደርግ እጅህንም ዘርግተህ ወደ እግዚአብሔር ብትጸልይ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነገር ግን ልብህን ብትሰጠው፣ እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥ እጆችህን ወደ እርሱ ትዘረጋለህ፥ በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፥ በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ልብህን ንጹሕ ብታደርግ፥ እጆችህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፥ በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፥ አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥ እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፥ |
ይህም ሁሉ ሆኖ አንዳንድ መልካም ነገር አድርገሃል፤ ይኸውም ሕዝቡ ያመልካት የነበረችውን አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስሎችን ሁሉ ከምድሪቱ አስወግደሃል፤ የእግዚአብሔርንም ፈቃድ ለይተህ ለመፈጸም ጥረት አድርገሃል።”
በችግር ጊዜ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ሌሊቱን ሙሉ ያለ ዕረፍት እጆቼን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ይሁን እንጂ ለመጽናናት አልቻልኩም።
እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ዐመፀኞችና እምቢተኞች አይሆኑም፤ እነዚያ እግዚአብሔርን በማመን የጸኑ አልነበሩም፤ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልኖሩም።
ሙሴም ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “ከከተማው እንደ ወጣሁ እጄን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነጐድጓዱም ይቆማል፤ በረዶም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም፤ በዚህ ዐይነት አንተም ምድር የእግዚአብሔር እንደ ሆነች ታውቃለህ።
ሳሙኤልም የእስራኤልን ሕዝብ፦ “በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ ባዕዳን አማልክትንና ዐስታሮትን ከእናንተ ዘንድ አስወግዱ፤ ራሳችሁንም ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ እግዚአብሔርም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድናችኋል” አላቸው።