ኢዮብ 10:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኔን በደል የምትመለከት፥ ኃጢአቴንም የምትከታተለው፥ ለምንድን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ፣ በደልን የምትፈላልግብኝ፣ ኀጢአቴንም የምትከታተለው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታዲያ ክፋቴን የምትከታተለው፥ ኃጢአቴንም የምትመረምረው ለምንድን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፋቴን ትፈላለግ ዘንድ፥ ኀጢኣቴንም ትመረምር ዘንድ፥ |
አንተ ሰዎችን በመቈጣጠር የምትከታተል አምላክ ሆይ፥ እኔ ኃጢአት በመሥራቴ አንተ ምን ተበደልክ? ስለምን ዒላማ አደረግኸኝ? ይህን ያኽል ከባድ ሸክም ሆንኩብህን?
ልብሶችሽ በንጹሖችና በድኾች ደም ተበክለዋል። “ነገር ግን ይህን ሁሉ አድርገሽ፥ ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤ በእርግጥ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አይቈጣም!’ ትያለሽ፤ ነገር ግን ‘እኔ ኃጢአት አልሠራሁም’ ብለሽ በመካድሽ ምክንያት እኔ እግዚአብሔር እፈርድብሻለሁ።
“በዚያን ቀን መብራት ይዤ ኢየሩሳሌምን እፈትሻለሁ፤ በመንደላቀቅ ኑሮ በአተላ ውስጥ አቅርሮ እንደ ቀረ የወይን ጠጅ የሆኑትንና ‘እግዚአብሔር በጎም ሆነ ክፉ ነገር አያደርግም’ የሚሉትን እቀጣለሁ።
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።