ኢዮብ 10:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕቢት ቢሰማኝ እንደ አንበሳ አድነህ ትይዘኛለህ፤ እኔንም ለመጒዳት መላልሰህ ታደርጋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሴን ከፍ ከፍ ባደርግ፣ እንደ አንበሳ ታደባብኛለህ፤ አስፈሪ ኀይልህን ደጋግመህ ታሳየኛለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሴም ከፍ ከፍ ቢል እንደ አንበሳ ታድነኛለህ፥ ተመልሰህም ድንቅ ነገር ታድርግብኛለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመገደል እንደ አንበሳ ታደንሁ። ተመልሰህም ፈጽመህ ታጠፋኛለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሴም ከፍ ከፍ ቢል እንደ አንበሳ ታድነኛለህ፥ ተመልሰህም ድንቅ ነገር ታድርግብኛለህ። |
ሕዝቡ ብዙ ጊዜ ዐምፀው እግዚአብሔርን ትተዋል፤ ስለዚህ ጠላቶቻቸው እንደ ዱር አንበሶች ወይም እንደ በረሓ ተኲላዎች አደጋ ይጥሉባቸዋል፤ እነዚያም ጠላቶች በከተሞቹ ላይ ሸምቀው ከዚያ የሚወጡትን ሰዎች ሁሉ እንደ ነብር ሆነው ይቦጫጭቁአቸዋል።
ከዚህ የተነሣ እስራኤልን እንደ አንበሳ፥ ይሁዳንም እንደ ደቦል አንበሳ በመሆን ሰባብሬአቸው እሄዳለሁ፤ ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።