ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።
ኢዮብ 1:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ አንተን የሚፈራህ እርሱንና ልጆቹን፥ ያለውንም ንብረት ሁሉ በደኅና ስለ ጠበቅህለት፥ የሚሠራውንም ሁሉ ስለ ባረክህለትና ብዙ የከብት መንጋ ስለ ሰጠኸው አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርሱና በቤተ ሰቦቹ፣ ባለው ንብረትስ ሁሉ ዙሪያ ዐጥር ሠርተህለት የለምን? የበጎቹና የላሞቹ መንጋ ምድርን ሁሉ እስኪሞሉ ድረስ የእጁን ሥራ ባርከህለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱንና ቤቱን በዙሪያውም ያሉትን ሁሉ አላጠርህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ንብረቱም በምድር ላይ በዝቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱንና ቤቱን በዙሪያውም ያሉትን ሁሉ አላጠርህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱም በምድር ላይ በዝቶአል። |
ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።
እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት የነበሩት መንጋዎችህ አሁን እጅግ በዝተዋል፤ እኔ በደረስኩበት ስፍራ ሁሉ እግዚአብሔር በረከትን ሰጥቶሃል፤ የምሠራውስ መቼ ለቤተሰቤ የሚጠቅም ነገር ነው?” አለው።
የአባትህ አምላክ ይረዳሃል፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ከላይ ከሰማይ ዝናብን፥ ከምድርም ጥልቀት ውሃን በመስጠት ይባርክሃል፤ ብዙ ከብትና ብዙ ልጆችም ይሰጥሃል።
በሀብትም በኩል ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና አምስት መቶ አህዮች ነበሩት፤ እንዲሁም እጅግ ብዙ አገልጋዮች ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ካሉት ሰዎች ሁሉ እርሱን የሚያኽል ሀብታምና ታላቅ ሰው አልነበረም።
እግሮቼ እንኳ በወተት እስኪታጠቡ ድረስ ብዙ ወተት አገኝ ነበር። የወይራ ዛፎቼም በጭንጫ መሬት ላይ እንኳ ተተክለው እንደ ጐርፍ የሚወርድ ብዙ ዘይት ይሰጡኝ ነበር።
እግዚአብሔር የኢዮብን የመጨረሻ ሕይወት ከመጀመሪያው አስበልጦ ባረከው፤ ስለዚህ ኢዮብ ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፤ ስድስት ሺህ ግመሎች፤ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፤ አንድ ሺህ እንስት አህዮች ነበሩት።
መሬቱን በመቈፈርና ድንጋዩንም ለቅሞ በማውጣት ምርጥ የሆነውን የወይን ሐረግ ተከለበት፤ በመካከሉም መጠበቂያ የሚሆን ማማ ሠራለት፤ ጒድጓድ ቆፍሮም የወይን ፍሬ መጭመቂያ አበጀለት። ከዚያን በኋላ መልካም ፍሬ ያፈራል ብሎ ጠበቀ፤ ነገር ግን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ።
“እንግዲህ በወይን ቦታዬ ላይ የማደርገውን ልንገራችሁ፤ በዙሪያው ያለውን አጥር ነቃቅዬ ቅጽሩን አፈርሳለሁ፤ የምድር አራዊት እንዲበሉትና እንዲፈነጩበት አደርጋለሁ።
እናንተን የሚነካ የእርሱን ዓይን ብሌን እንደሚነካ ሆኖ ይቈጠራል። የክብር ጌታ በበዘበዙአችሁ ሕዝቦች ላይ በላከኝ ጊዜ የተናገራቸው ቃላት እነዚህ ናቸው።
እርሱ አንተን ይወድሃል፤ ይባርክህማል፤ ስለዚህም በቊጥር ትበዛለህ፤ የምትወልዳቸው ልጆች ይባረካሉ፤ የምድርህም ፍሬ ይባረካል፤ ስለዚህም ብዙ እህል፥ ወይንና የወይራ ዘይት ታገኛለህ፤ ከዚህም ጋር ብዙ የከብትና የበግ መንጋ ያበዛልሃል፤ ለአንተ ይሰጥህ ዘንድ ለቀድሞ አባቶችህ ተስፋ በሰጠው ምድር ላይ ይህን ሁሉ በረከት ይሰጥሃል።