ባቢሎንን ረግረግ ስለማደርጋት የአልቅት መፈልፈያ ትሆናለች፤ ባቢሎንን ሁሉን ነገር ጠራርጎ በሚወስድ መጥረጊያ እጠርጋታለሁ፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”
ኤርምያስ 49:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ሐጾር ለዘለዓለሙ ቀበሮዎች ብቻ የሚኖሩባት ምድረ በዳ ሆና ትቀራለች፤ ዳግመኛም በዚያ ሰፍሮ የሚኖር ሕዝብ ከቶ አይገኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሐጾር የቀበሮዎች መፈንጫ፣ ለዘላለም ባድማ ትሆናለች፤ ማንም በዚያ አይኖርም፤ የሚቀመጥባትም አይገኝም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሦርም የቀበሮዎች መኖሪያና የዘለዓለም ባድማ ትሆናለች፤ በዚያም ማንም ሰው አይኖርም፥ የሰው ልጅም አይቀመጥባትም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሦርም የወፎች መኖሪያና የዘለዓለም ባድማ ትሆናለች፤ በዚያም ሰው አይኖርም፤ የሰው ልጅም አይቀመጥባትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሶርም የቀበሮ መኖሪያና የዘላለም ባድማ ትሆናለች፥ በዚያም ሰው አይኖርም፥ የሰው ልጅም አይቀመጥባትም። |
ባቢሎንን ረግረግ ስለማደርጋት የአልቅት መፈልፈያ ትሆናለች፤ ባቢሎንን ሁሉን ነገር ጠራርጎ በሚወስድ መጥረጊያ እጠርጋታለሁ፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”
አድምጡ አዲስ ዜና መጥቶአል! የሰሜን መንግሥት የይሁዳን ከተሞች ወደ ምድረበዳነት ለውጦ የቀበሮዎች መመሰጊያ ለማድረግ በመራወጥ ላይ ይገኛል።”
ያቺ አገር የፍርስራሽ ክምርና የቀበሮዎች መፈንጫ ትሆናለች፤ ለማየትም የምታሰቅቅ ትሆናለች፤ ማንም አይኖርባትም፤ የሚያያትም ሁሉ ይሳለቅባታል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር አደርጋታለሁ፤ የቀበሮዎችም መፈንጫ ትሆናለች፤ የይሁዳንም ከተሞች ማንም የማይኖርባቸው ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”
እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ፥ ሞአብ እንደ ሰዶም አሞንም እንደ ገሞራ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም በዳዋና በጨው ጒድጓድ ተወራ ለዘለቄታ ባድማ ትሆናለች፤ ከሞት የተረፈው ሕዝቤ ይበዘብዛቸዋል ንብረታቸውንም ይወርሳል።”
ከፍ ባለ ድምፅም እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ ሆነች! የርኩሳን መናፍስት ማደሪያ ሆነች! የሚያጸይፉና የሚያስጠሉ ወፎች መጠለያ ሆነች!