ኤርምያስ 46:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግብጽ ሕዝብ በሰሜን ሕዝብ ስለሚሸነፉ ያፍራሉ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የግብጽ ሴት ልጅ ለኀፍረት ትጋለጣለች፤ ለሰሜን ሕዝብም ዐልፋ ትሰጣለች።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የግብጽ ሴት ልጅ ታፍራለች፤ ለሰሜኑ ሕዝብ ተላልፋ በእጃቸው ትሰጣለች።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የግብፅ ልጅ ታፍራለች፤ በሰሜን ሕዝብ እጅም አልፋ ትሰጣለች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የግብጽ ልጅ ታፍራለች፥ በሰሜን ሕዝብ እጅ አልፋ ትሰጣለች። |
በስተ ሰሜን የሚኖሩ ሕዝቦች ወደዚህ እንዲመጡ እጠራለሁ፤ ኢየሩሳሌምንና በዙሪያዋ ያሉትን የይሁዳ ከተሞች አደጋ ጥለው ይይዙአቸዋል፤ ከዚያም በኢየሩሳሌም መግቢያ በር ላይ ዙፋናቸውን ይዘረጋሉ።
እንደ ድንግል የምትታዪ ግብጽ ሆይ! ወደ ገለዓድ ሄደሽ የሚቀባ መድኃኒት ፈልጊ፤ የአንቺ መድኃኒት ሁሉ ከንቱ ነው፤ ሊፈውስሽ የሚችል ነገር ከቶ የለም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ውሃ ከሰሜን በኩል ተነሥቶ በጐርፍ እንደ ተሞላ ወንዝ ይፈስሳል፤ ምድርንና በምድር ላይ ያለውን ሁሉ ከተሞችንና በውስጣቸው የሚኖሩትን ሕዝብ በሙሉ ይሸፍናል። ሕዝቡ ሁሉ ርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ምርር ብለው ያለቅሳሉ።