ኤርምያስ 46:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀያል ነው የምትሉት አጲስ የተባለው ጣዖት ስለምን ወደቀ? እግዚአብሔር ገፍቶ ስለ ጣለው አይደለምን?’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጦረኞችህ ለምን ተዘረሩ? እግዚአብሔር ገፍትሮ ስለሚጥላቸው መቆም አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃይለኞችህ ስለምን ተወገዱ? ጌታ ገፍቶአቸዋልና አልቆሙም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀይለኞችህ ስለ ምን ታጡ? እግዚአብሔር ስላደከማቸው የሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃይለኞችህ ስለ ምን ተወገዱ? እግዚአብሔር ስላደከማቸው አልቆሙም። |
በቀድሞ ዘመን እጆችህ ያደረጉትን ድርጊት ሁሉ አባቶቻችን ነግረውናል፤ ይኸውም፥ እነርሱን ለመትከል ሕዝቦችን አባረሃል፤ እነርሱን ለማደላደል ነዋሪዎቹን አጥፍተሃል።
እግዚአብሔርም ሙሴን “በንጉሡ በፈርዖን ላይ የማደርገውን አሁን ታያለህ፤ በኀይሌ ተገዶ ሕዝቤን ይለቃል፤ በኀያል ክንዴም ተሸንፎ ያባርራቸዋል።”
ቅጥረኞች ወታደሮችዋም እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤ ወደ ኋላ ተመልሰው ይሸሻሉ፤ የፍርድና የጥፋት ቀን ስለ ደረሰባቸው፥ ጸንተው መዋጋት አይችሉም።
“ነገር ግን ይህ የማየው ነገር ምንድን ነው? ከፍርሃት የተነሣ ወደ ኋላ በመመለስ ላይ ናቸው፤ ወታደሮቻቸው ድል ሆኑ፤ በየአቅጣጫው ፍርሀትና ሽብር ስላለ ወደ ኋላ መለስ ብለው ሳያዩም ወደ ፊት ሸሹ።
ይህን ብታደርጉ እግዚአብሔር እነዚህን በፊታችሁ ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ ያስወጣል፤ እናንተም በብዛትና በኀይል ከእናንተ እጅግ ብርቱዎች የሆኑትን ሕዝቦች ምድር ትወርሳላችሁ።