ራሳቸው የሚሰጡትም መልስ ‘የእስራኤል ሕዝብ የቀድሞ አባቶቻቸውን ከግብጽ ምድር ያወጣ አምላካቸውን እግዚአብሔርን በመተዋቸው ምክንያት ነው፤ ከዚህም በቀር ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት ትተው ሌሎችን አማልክት አመለኩ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ የጥፋት መቅሠፍት ያመጣባቸውም ስለዚህ ነው’ የሚል ነው።”
ኤርምያስ 44:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሁሉ መቅሠፍት የደረሰባችሁ ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት በማቅረባችሁ፥ እግዚአብሔርን በማሳዘናችሁ፥ ለሕጉ፥ ለድንጋጌውና ለሥርዓቱም ባለመታዘዛችሁ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕጣን በማጠን በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ስለ ሠራችሁና ቃሉን ስላልጠበቃችሁ ሕጉን፣ ሥርዐቱንና ትእዛዙን ስላላከበራችሁ ዛሬ እንደምታዩት ጥፋት መጥቶባችኋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስላጠናችሁ፥ በጌታም ላይ ኃጢአትን ስለ ሠራችሁ፥ የጌታንም ድምፅ ስላልሰማችሁ፥ በሕጉና በሥርዓቱም በምስክሩም ስላልሄዳችሁ፥ ስለዚህ ዛሬ እንደሆነ ይህ ክፉ ነገር ደርሶባችኋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስላጠናችሁት ዕጣን፥ በእግዚአብሔርም ላይ ስለ በደላችሁ፥ የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልሰማችሁ፥ በሕጉና በሥርዐቱም፥ በምስክሩም ስላልሄዳችሁ፥ ስለዚህ ዛሬ እንደ ሆነ ይች ክፉ ነገር አግኝታችኋለች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስላጠናችሁ፥ በእግዚአብሔርም ላይ ስለ በደላችሁ፥ የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልሰማችሁ፥ በሕጉና በሥርዓቱም በምስክሩም ስላልሄዳችሁ፥ ስለዚህ ዛሬ እንደ ሆነ ይህች ክፉ ነገር አግኝታችኋለች። |
ራሳቸው የሚሰጡትም መልስ ‘የእስራኤል ሕዝብ የቀድሞ አባቶቻቸውን ከግብጽ ምድር ያወጣ አምላካቸውን እግዚአብሔርን በመተዋቸው ምክንያት ነው፤ ከዚህም በቀር ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት ትተው ሌሎችን አማልክት አመለኩ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ የጥፋት መቅሠፍት ያመጣባቸውም ስለዚህ ነው’ የሚል ነው።”
የሰጣቸውንም ድንጋጌ አልተቀበሉም፤ ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ የሰጣቸውንም ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ቸል አሉ፤ ለከንቱ ጣዖቶች በመስገድ ራሳቸውም ከንቱዎች ሆኑ፤ የእነርሱን መጥፎ ምሳሌነት እንዳይወርሱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዝ በመሻር በዙሪያቸው የሚኖሩ የአሕዛብን ልማድ ሁሉ ተከተሉ።
እስራኤላውያን ግን በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሳለቁ፤ በነቢያቱም በማፌዝ፥ የእግዚአብሔርን ቃል አቃለሉ፤ ከዚህም የተነሣ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ በሕዝቡ ላይ ወረደ፤ ከታላቅ ቊጣውም ለማምለጥ አልቻሉም።
አምላካችን በእኛና በከተማይቱ ላይ ይህን ጥፋት ያመጣው የቀድሞ አባቶቻችሁ ይህን ጥፋት ስላደረጉ አይደለምን? አሁንም እናንተ ሰንበትን ባለማክበራችሁ የእግዚአብሔርን ቊጣ በእስራኤል ላይ ታነሣሣላችሁ።”
አደርጋለሁ ብሎ ያቀደውን ሁሉ እነሆ አሁን ፈጽሞታል፤ ይህም ሁሉ የሆነው እናንተ ኃጢአት በመሥራታችሁና ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛችሁ ምክንያት ነው።
ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ራሳችሁን ዝቅ በማድረግ ትሑታን ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ ለእኔ ክብር አልሰጣችሁኝም፤ ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለእናንተ በሰጠሁትም ሕግና ደንብ ጸንታችሁ መኖር አልፈለጋችሁም።
ነገር ግን ለሰማይ ንግሥት የሚቃጠል መሥዋዕትና ለእርስዋም የወይን ጠጅ መባ ማቅረብን ካቋረጥንበት ጊዜ ጀምሮ ምንም ያተረፍነው ነገር የለም፤ ሕዝባችንም በጦርነትና በረሀብ አልቆአል።”
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “በኢየሩሳሌምና በሌሎችም የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ያመጣሁትን ጥፋት እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል፤ አሁንም እንኳ እንደ ፈራረሱ ናቸው፤ ማንም አይኖርባቸውም፤
“እናንተና የቀድሞ አባቶቻችሁ፥ ንጉሦቻችሁና መሪዎቻችሁ፥ በምድሪቱም የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ዕጣን ታጥኑ እንደ ነበረ፥ እግዚአብሔር አያስበውም ወይም ረስቶታል ብላችሁ ታስባላችሁን?
ይህም የሆነበት ምክንያት በእነዚያ ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ሕዝብ ክፉ ሥራ በመሥራት ስላስቈጡኝ ነው፤ እነርሱ ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት አቀረቡ፤ እነርሱም ሆኑ እናንተ ወይም የቀድሞ አባቶቻችሁ ያላመለኩአቸውን አማልክት አመለኩ፤
መጥታችሁ በምትኖሩባት በዚህችስ በግብጽ ምድር ለጣዖቶች በመስገድና ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት በማቅረብ ስለምን ታስቈጡኛላችሁ? ወይስ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እንዲዘባበቱባችሁና ስማችሁንም መራገሚያ ያደርጉት ዘንድ ራሳችሁን በራሳችሁ ማጥፋት ትፈልጋላችሁን?
ኢየሩሳሌም ከባድ ኃጢአት ሠርታለች፤ መሳለቂያም ሆናለች፤ ዕርቃንዋን ስላዩአት የሚያከብሩአት ሁሉ ይንቁአታል፤ እርስዋ ራስዋ እየቃተተች ፊትዋን ታዞራለች።
በሙሴ ሕግ በተጻፈው መሠረት ይህን ሁሉ መከራ በእኛ ላይ አመጣህ፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፥ ይህም ሁሉ ሆኖ ከኃጢአታችን በመመለስና እውነትን በመከተል የአንተን ምሕረት ለማግኘት ወደ አንተ አልጸለይንም።
አይደለም! አሕዛብ መሥዋዕት የሚያቀርቡት ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለአጋንንት ነው፤ ስለዚህ እናንተ ከአጋንንት ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አልፈልግም፤
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖቶች ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔርም፦ “መኖሪያዬን በሕዝቤ መካከል አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር እኖራለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ” ብሎ እንደ ተናገረው እኛ እያንዳንዳችን የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን።