La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 44:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሴቶችም ጨምረው ሲናገሩ፥ “በሰማይ ንግሥት እንጎቻ በምንጋግርበት ጊዜ፥ ለእርስዋ መሥዋዕትና የወይን ጠጅ መባ በምናቀርብበት ጊዜ፥ ከባሎቻችን ተለይተን ያደረግነው ነገር አልነበረም።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሴቶቹም፣ “ለሰማይዋ ንግሥት በምናጥንበትና የመጠጥ ቍርባን በምናፈስስበት ጊዜ፣ በምስሏ ዕንጐቻ ስንጋግርና የመጠጥ ቍርባን ስናፈስስላት ባሎቻችን አያውቁም ነበርን?” አሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኛስ ለሰማይ ንግሥት ባጠንንላት የመጠጥንም ቁርባን ባፈሰስንላት ጊዜ፥ በውኑ ያለ ባሎቻችን ፈቃድ ምስልዋ ያለበት እንጐቻ አድርገንላታልን? የመጠጥንስ ቁርባን አፍስሰንላታልን?”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኛስ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት ባጠ​ን​ን​ላት፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን ባፈ​ሰ​ስ​ን​ላት ጊዜ፥ በውኑ ያለ ባሎ​ቻ​ችን ምስ​ል​ዋን ለማ​በ​ጀት እን​ጎቻ አድ​ር​ገ​ን​ላት ኖሮ​አ​ልን? የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን አፍ​ስ​ሰ​ን​ላት ኖሮ​አ​ልን?”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኛስ ለሰማይ ንግሥት ባጠንንላት የመጠጥንም ቍርባን ባፈሰስንላት ጊዜ፥ በውኑ ያለ ባሎቻችን ምስልዋን ለማበጀት እንጐቻ አድርገንላት ኖሮአልን? የመጠጥንም ቍርባን አፍስሰንላት ኖሮአልን?

Ver Capítulo



ኤርምያስ 44:19
14 Referencias Cruzadas  

ሴቲቱም ዛፉ የሚያምር፥ ፍሬውም ለመብላት የሚያስጐመዥና ጥበብን የሚያስገኝ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ለባሏም ከፍሬው ሰጠችው፤ እርሱም በላ።


በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር በማድረግ ሁለንተናውን ለኃጢአት አሳልፎ የሸጠ አክዓብን የሚምስል ማንም አልነበረም፤ ይህን ሁሉ ለማድረግ የተገደደው ሚስቱ ኤልዛቤል ወደ ክፋት ስለ መራችው ነው፤


ከአክዓብ ሴቶች ልጆች አንዲቱን በማግባቱ፥ የንጉሥ አክዓብንና የሌሎቹን የእስራኤል ነገሥታት መጥፎ ምሳሌነት ተከትሎ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአትን ሠራ፤


በእርግጥ ክፉ ሰዎች መቀጣታቸው የማይቀር ነው፤ ደጎች ግን ይድናሉ።


ሚስቶቻቸው ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት የሚያቀርቡ መሆናቸውን የሚያውቁ ወንዶች ሁሉ፥ በግብጽ ደቡባዊ ክፍል የሚኖሩት እስራኤላውያንና በዚያ ቆመው የነበሩት ሴቶች ሁሉ በአንድነት ተሰብስበው በመቅረብ እንዲህ አሉኝ፦


በዚህ ዐይነት የመለሱልኝን ወንዶች፥ ሴቶችና ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አልኳቸው፦


ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፤ አባቶች እሳት ያቀጣጥላሉ፤ ሴቶች ‘የሰማይ ንግሥት’ ለተባለችው ጣዖት ኅብስት ለመጋገር ሊጥ ያቦካሉ፤ እኔንም ለማስቈጣት ለሌሎች አማልክት የወይን ጠጅ መባ ያቀርባሉ።


ባልዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ስእለትዋን እንዳትፈጽም ቢከለክላት ግን የመፈጸም ግዴታ የለባትም፤ ስእለትዋን ለመፈጸም ያልቻለችው ባልዋ ስለ ከለከላት በመሆኑ እግዚአብሔር ይቅርታ ያደርግላታል።


ባልዋ ስለ ጉዳዩ ሰምቶ ከከለከላት ግን የመፈጸም ግዴታ የለባትም፤ ስእለትዋን ለመፈጸም ያልቻለችው ባልዋ ስለ ከለከላት በመሆኑ እግዚአብሔር ይቅርታ ያደርግላታል።