ኢሳይያስ 64:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤ የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፤ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ በኀጢአታችን ምክንያት እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ እንዲሁም ነፋስ ጠራርጎ ወስዶናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፥ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል። |
“ጌታ ሆይ! እኔ ለምንም የማልጠቅም ከንቱ ሰው ነኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ አፌን በእጄ ይዤ ዝም ከማለት በስተቀር፥ ለአንተ የምሰጠው መልስ የለኝም።
“እግዚአብሔር ክፉ አድራጊዎች ከቶ አያስተውሉምን? ሰዎች እንጀራን እንደሚበሉ ክፉ አድራጊዎች ሕዝቤን ይበዘብዛሉ፤ እነርሱም ወደ እኔ ወደ እግዚአብሔር አይጸልዩም።” ይላል።
በእስራኤል ስም የምትጠሩ፥ ከይሁዳ ወገን የሆናችሁ፥ እናንተ የያዕቆብ ልጆች! ይህን ስሙ። እናንተ በታማኝነትና በእውነት ሳይሆን፥ የእስራኤልን አምላክ እናመልካለን ትላላችሁ፤ በእግዚአብሔር ስምም ትምላላችሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወንድ ሚስቱን ፈቶ እንደሚያባርር እኔ እናንተን ሕዝቤን ያባረርኩ ይመስላችኋልን? ይህስ ከሆነ የፍችው ደብዳቤ የት አለ? ሰው ልጆቹን ለባርነት እንደሚሸጥ እኔም እናንተን ለምርኮ አሳልፌ የሸጥኳችሁ ይመስላችኋልን? ከሆነስ ለማንኛውም አበዳሪዬ ሸጥኳችሁ? እናንተ ለምርኮ የተሰጣችሁት በኃጢአታችሁ ምክንያት ነው፤ የተሰደዳችሁትም በፈጸማችሁት በደል ነው።
“እኔ በመጣሁ ጊዜ ማንም ሰው አለመኖሩ ለምንድን ነው? በጠራሁም ጊዜ ማንም ሰው መልስ ያልሰጠኝ ለምንድን ነው? እኔ ለመታደግ አልችልምን? ለማዳንስ ኀይል የለኝምን? በተግሣጼ ብቻ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ወደ ምድረ በዳነት እለውጣለሁ፤ ዓሣዎቻቸውም ውሃ ከማጣት የተነሣ ሞተው ይበሰብሳሉ።
ሁላችንም እንደ በጎች ባዝነን ነበር፤ ሁላችንም ወደ ራሳችን መንገድ ሄደን ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
እኔም “እነሆ አንደበቶቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል የምኖር፥ አንደበቴም የረከሰብኝ ሰው ነኝ፤ ንጉሡን የሠራዊት አምላክን በዐይኖቼ አይቼአለሁና መጥፋቴ ስለ ሆነ ወዮልኝ!” አልኩ።
በሙሴ ሕግ በተጻፈው መሠረት ይህን ሁሉ መከራ በእኛ ላይ አመጣህ፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፥ ይህም ሁሉ ሆኖ ከኃጢአታችን በመመለስና እውነትን በመከተል የአንተን ምሕረት ለማግኘት ወደ አንተ አልጸለይንም።
“ሁሉም በቊጣ እንደ ምድጃ ግለው ገዢዎቻቸውን ፈጁ፤ ንጉሦቻቸውንም በየተራ አጠፉ፤ ይህም ሁሉ ሲሆን ከእነርሱ አንድ እንኳ የእኔን ርዳታ የጠየቀ የለም።”
በእኔ ወይም በእኔ ሥጋዊ ባሕርይ ምንም መልካም ነገር እንደሌለ ዐውቃለሁ፤ መልካም ነገርን የማድረግ ፍላጎት ቢኖረኝም እንኳ ያን መልካም ነገር ለማድረግ ችሎታ የለኝም።
ይህንንም የማደርግበት ምክንያት በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴን ጽድቅ ትቼ በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ በክርስቶስ በማመን ለማግኘትና ከእርሱም ጋር ለመሆን ነው።
እኛም ከዚህ በፊት ሞኞች፥ የማንታዘዝ እምቢተኞች፥ መንገዳችንን የሳትን ተላላዎች፥ ለልዩ ልዩ ፍትወትና ሥጋዊ ደስታ የተገዛን፥ በተንኰልና በምቀኝነት የምንኖር፥ የተጠላንና እርስ በርሳችንም የምንጣላ ነበርን።