ኢሳይያስ 64:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀድሞ አባቶቻችን አንተን ሲያመሰግኑበት የነበረ፥ ቅዱስና ውብ የሆነው ቤተ መቅደስህ በእሳት ጋይቶአል፤ የሚያስደስቱ ነገሮች ሁሉ ፈራርሰዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰውና የተከበረው ቤተ መቅደሳችን፣ በእሳት ተቃጥሏል፤ ያማሩ ቦታዎቻችንም ሁሉ እንዳልነበር ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰና የተዋበ ቤታችን በእሳት ተቃጥሎአል፤ ያማረውም ስፍራችን ሁሉ ፈራርሷል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቶቻችን ያከበሩት ክብራችን ቤተ መቅደስህ በእሳት ተቃጥሎአል፤ ያማረውም ስፍራችን ፈርሶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰና የተዋበ ቤታችን በእሳት ተቃጥሎአል፥ ያማረውም ስፍራችን ሁሉ ፈርሶአል። |
“በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለሕዝቡ ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠውም መልካም ተስፋ ምንም የቀረ የለም።
እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! እርሱ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠውን የተስፋ ቃል ፈጽሞአል፤ የሰጠውም የተስፋ ቃል እንዲህ የሚል ነው፦
እስራኤላውያን እሳት ከሰማይ ሲወርድና የእግዚአብሔርም ክብር በቤተ መቅደስ ላይ ማረፉን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው፦ “እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነው!” እያሉ ሰገዱ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ።
ካህናቱም በተመደበላቸው ቦታ ቆሙ፤ ከእነርሱም ፊት ለፊት ሌዋውያን ቆመው አስቀድሞ ንጉሥ ዳዊት አሠርቶ እግዚአብሔርን ለማመስገን ይጠቀምባቸው በነበሩት የዜማ መሣሪያዎች ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ እያሉ በመዘመር እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ካህናቱም መለከት ሲነፉ እስራኤላውያን ሁሉ ቆመው ነበር።
የኢየሩሳሌም ሕዝብ በቀድሞ ጊዜ የነበሩአቸውን የከበሩ ነገሮች በችግራቸውና በጭንቀታቸው ቀን ያስታውሳሉ፤ እነርሱም በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ፥ አንድም ረዳት ባልነበራቸው ጊዜ፥ ጠላቶቻቸው የከተማቸውን ውድቀት ተመልክተው ተሳለቁባቸው።
እግዚአብሔር በቊጣው ጽዮንን ምንኛ አዋረዳት! ወደ ሰማይ ከፍ ብላ የነበረችውን የእስራኤልን መመኪያ ወደ ምድር ጣላት፤ በቊጣው ቀን የእግሩ ማሳረፊያ መሆንዋን ሊያስታውስ አልፈቀደም።
እግዚአብሔር መሠዊያውን ናቀ፤ መቅደሱንም ተወ፤ የቤተ መንግሥቶችዋን ቅጽሮች ለጠላት አሳልፎ ሰጠ፤ በበዓላት ቀን እንደሚደረገው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከፍተኛ ድምፅ ተሰማ።
‘ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው አለኝ፤ የክብራችሁ ትምክሕት፥ የዐይናችሁ ተስፋና የልባችሁ ደስታ የሆነውን ቤተ መቅደሴን እንዲያረክሱ እተዋቸዋለሁ፤ በኢየሩሳሌም የቀሩት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በጦርነት ይገደላሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አሁንም የሰው ልጅ ሆይ! ዘወትር ሊያዩትና ሊጐበኙት የሚወዱትን፥ የሚመኩበትንና የሚደሰቱበትን እጅግ ጽኑ የሆነውን ቤተ መቅደስ ከእነርሱ እወስድባቸዋለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም እወስዳለሁ።
መልአኩም “የሠራዊት አምላክ ሆይ! ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ሁሉ ከተቈጣህ እነሆ ሰባ ዓመቶች አለፉ፤ ምሕረት የማታደርግላቸው እስከ መቼ ነው?” ሲል ጠየቀ።
ምድሪቱም ሁሉ በዲንና በጨው ትሸፈናለች፤ ምንም ነገር አይተከልባትም፤ ምንም ነገር አታበቅልም፤ እግዚአብሔር በኀይለኛ ቊጣው እንደ ደመሰሳቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ጺባዮ ትሆናለች።