እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።”
ኢሳይያስ 63:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በችግራቸው ጊዜ ሁሉ ያዳናቸው በመልእክተኛ ወይም በመልአክ አማካይነት ሳይሆን እርሱ በመካከላቸው በመገኘት ነው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ታደጋቸው፤ እርሱም በቀድሞ ዘመናት ሁሉ አንሥቶ ልጁን እንደሚሸከም ሰው ተንከባከባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጭንቃቸው ሁሉ ተጨነቀ፤ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በምሕረቱ ዋጃቸው፤ በቀደመው ዘመን ሁሉ አነሣቸው፤ ተሸከማቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመልእክተኛም አይደለም፤ በመልአክም አይደለም፤ እርሱ ራሱ ያድናቸዋል እንጂ። እርሱ ይወዳቸዋልና፥ ይራራላቸዋልምና እርሱ ተቤዣቸው፤ ተቀበላቸውም፤ በዘመናቸውም ሁሉ ለዘለዓለም አከበራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፥ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው። |
እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።”
ሆኖም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ምሕረትን አደረገ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር አላቸው እንጂ አላጠፋቸውም። ብዙ ጊዜ ቊጣውን መለሰ፤ ብዙ ጊዜም መዓቱን ገታ።
የእስራኤልን ሠራዊት ፊት ፊት ይመራ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ኋላ ተመልሶ ደጀን ሆነ፤ የደመናውም ዐምድ አልፎ በኋላ በኩል ቆመ፤
“ ‘እኔ እግዚአብሔር በግብጻውያን ላይ ያደረግኹትንና ንስር ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ እንደምትሸከም እኔም እናንተን እስከዚህ ስፍራ እንዴት ወደ እኔ እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል፤
የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! የፈጠራችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የታደግኋችሁ ስለ ሆነ አትፍሩ፤ እናንተ የእኔ ናችሁ፤ በስማችሁም ጠርቼአችኋለሁ።
እንግዲህ ከባቢሎን ወጥታችሁ ሽሹ፤ “እግዚአብሔር አገልጋዩን እስራኤልን አድኖአል” የሚለውን የምሥራች ቃል በደስታ አብሥሩ፤ በየስፍራውም እንዲታወቅ አድርጉ።
አንበሶቹ እንዳይጐዱኝ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ አፋቸውን ዘጋ፤ ይህንንም ያደረገው እኔ በእርሱ ዘንድ ንጹሕ መሆኔንና አንተንም አለመበደሌን ስላወቀ ነው።”
ለይሁዳ ሕዝቦች ግን ፍቅር አሳያቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ፤ የማድናቸውም በጦርነት ኀይል አይደለም፤ በሰይፍ፥ በቀስትና በፍላጻ ወይም በፈረስና በፈረሰኛ አይደለም።”
እናንተን የሚነካ የእርሱን ዓይን ብሌን እንደሚነካ ሆኖ ይቈጠራል። የክብር ጌታ በበዘበዙአችሁ ሕዝቦች ላይ በላከኝ ጊዜ የተናገራቸው ቃላት እነዚህ ናቸው።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ በፊቴ መንገድን ያዘጋጅ ዘንድ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ የምትፈልጉት ጌታም በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤ በእርሱ የምትደሰቱበት የቃል ኪዳን መልእክተኛም በእርግጥ ይመጣል።”
ንጉሡም ‘በእውነት እላችኋለሁ፤ ከእነዚህ ከወንድሞቼ አነስተኛ ለሆነው ለአንዱ እንኳ ያደረጋችኹት ሁሉ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው!’ ሲል ይመልስላቸዋል።
ንጉሡም ‘በእውነት እላችኋለሁ፤ ከእነዚህ ከወንድሞቼ አነስተኛ ለሆነው ለአንዱ እንኳ ያላደረጋችሁት ሁሉ ለእኔ እንዳላደረጋችሁት ነው’ ይላቸዋል።
ጴጥሮስም ወደ ልቡናው ተመልሶ፥ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠባበቁት ከነበረው ነገር ሁሉ ያዳነኝ መሆኑን አሁን ገና በእውነት ዐወቅሁ!” አለ።
በበረሓ ተሰብስቦ ከነበረው ሕዝብ ጋርና ከሲና ተራራ ላይ ከተናገረው መልአክ ጋር እንዲሁም ከአባቶቻችን ጋር የነበረው እርሱ ነው። የእግዚአብሔርን የሕይወት ቃል ለእኛ ያስተላለፈልንም ይኸው ሙሴ ነው።
እናንተ ወደዚህ ቦታ እስክትመጡ ድረስ አንድ ሰው ልጁን እንደሚንከባከብ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ አምላካችሁ እግዚአብሔር በምድረ በዳው እንደ ተንከባከባችሁ አይታችኋል።’
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።
አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥ ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥ አንተ ስለ ታረድህ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤