ምንም እንኳ የእስራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ቢሆንም ከእነርሱ መካከል የሚድኑት የተረፉት ብቻ ናቸው፤ ለሕዝቡ ጥፋት ተገቢ የሆነ እውነተኛ ፍርድ ተዘጋጅቶአል።
ኢሳይያስ 60:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱ ጥቂቶቹ በሺህ የሚቈጠር ብዛት ይኖራቸዋል፤ ከእነርሱም ደካሞች የነበሩት ኀያል ሕዝብ ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ጉዳይ በጊዜው ፈጥኖ እንዲፈጸም አደርጋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአንቺ ታናሽ የሆነው ሺሕ፣ ከሁሉም የመጨረሻው ታናሽ ኀያል መንግሥት ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ጊዜውም ሲደርስ ይህን በፍጥነት አደርጋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታናሹ ለሺህ፥ የሁሉም ታናሹ ኃያል መንግሥት ይሆናል፤ እኔ ጌታ በዘመኑ ይህን በፍጥነት አደርገዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታናሹ ሺህ፥ የሁሉም ታናሽ ታላቅ ሕዝብ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር በዘመናቸው ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታናሹ ለሺህ የሁሉም ታናሹ ለብርቱ ሕዝብ ይሆናል፥ እኔ እግዚአብሔር በዘመኑ ይህን አፋጥነዋለሁ። |
ምንም እንኳ የእስራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ቢሆንም ከእነርሱ መካከል የሚድኑት የተረፉት ብቻ ናቸው፤ ለሕዝቡ ጥፋት ተገቢ የሆነ እውነተኛ ፍርድ ተዘጋጅቶአል።
“እኛ በዐይናችን እናያት ዘንድ እግዚአብሔር ሊያደርግ ያቀደውን በፍጥነት ያድርግ፤ እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ ያቀዳት ምክር ትፈጸም” ለሚሉ ሁሉ ወዮላቸው!
ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃምና ወደ ወለደቻችሁ ወደ ሣራ ተመልከቱ፤ አብርሃምን በጠራሁት ጊዜ ልጅ አልነበረውም፤ ነገር ግን እኔ ባረክሁት፤ ዘሩንም አበዛሁለት።
እንዲህ ያለ ነገር የሰማ እንዲህ ያሉ ነገሮችን ያየ ማነው? አንድ አገር በአንድ ቀን፥ አንድ ሕዝብ በቅጽበት ሊወለዱ ይችላሉን? ይሁን እንጂ ጽዮን ምጥ እንደ ያዛት ወዲያውኑ ልጆችዋን ወልዳለች።
ብረቱ፥ ሸክላው፥ ነሐሱ፥ ብሩና ወርቁ ሁሉ ወዲያውኑ ተንከታክቶ በበጋ ወራት በአውድማ ላይ እንደሚገኝ እብቅ ሆነ፤ ምንም ሳያስቀር ነፋስ ጠራርጎ ወሰደው፤ በምስሉ ላይ የወደቀው ድንጋይ ግን ምድርን ሁሉ እስኪሞላ ድረስ ከፍ ከፍ ብሎ ታላቅ ተራራ ሆነ።
በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይፈርስና ግዛቱም በሌላ ሕዝብ የማይደፈር መንግሥትን ይመሠርታል፤ ይህ መንግሥት ሌሎችን መንግሥታት እስከ መጨረሻው ያጠፋቸዋል፤ እርሱ ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤
አንካሶች ተርፈው እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ ተጥለው የነበሩትን ብርቱ ሕዝብ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔም በጽዮን ተራራ ላይ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም በእነርሱ ላይ እነግሣለሁ።”
ምክንያቱም ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ይጠብቃል፤ እርሱም የሚናገረው የሚፈጸምበትን ቀን ነው፤ ሐሰትም የለበትም፤ ጊዜ የሚወስድ ቢመስልም ጠብቅ፤ በእርግጥ ይደርሳል፤ አይዘገይምም።
ከዚህ በኋላ ተመለከትኩ፤ እጅግ ብዙ ሰዎችን አየሁ፤ እነርሱ ከሕዝብና ከነገድ፥ ከወገንና ልዩ ልዩ ቋንቋ ከሚናገሩ ሁሉ የተውጣጡ ነበሩ፤ እነዚህ ነጭ ልብስ ለብሰው፥ የዘንባባ ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆመው ነበር፤