የእኔ ሕዝብ አደርጋችኋለሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤ ከግብጽ ባርነትም ነጻ በማወጣችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ መሆኔን ታውቃላችሁ፤
ኢሳይያስ 60:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆች የእናታቸውን ጡት እንደሚጠቡ የአንቺም ልጆች የሕዝቦችንና የነገሥታትን ሀብት በመውሰድ ይጠቀሙበታል፤ አንቺም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ ኀያሉ የያዕቆብ አምላክ መሆኔን ታውቂአለሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመንግሥታትን ወተት ትጠጪያለሽ፤ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽ፣ ቤዛሽም እኔ የያዕቆብ ኀያል እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሕዛብንም ወተት ትጠጫልሽ፥ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ እኔም ጌታ፥ የያዕቆብ ኃያል፥ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ እንደሆንሁ ታውቂያለሽ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሕዛብንም ወተት ትጠጫለሽ፤ የነገሥታትንም ብልጽግና ትበያለሽ፤ እኔም እግዚአብሔር የእስራኤል ቅዱስ፥ መድኀኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሕዛብንም ወተት ትጠጫልሽ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፥ እኔም እግዚአብሔር የያዕቆብ ኃያል፥ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ። |
የእኔ ሕዝብ አደርጋችኋለሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤ ከግብጽ ባርነትም ነጻ በማወጣችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ መሆኔን ታውቃላችሁ፤
እነርሱም የሠራዊት አምላክ በግብጽ ምድር ለመኖሩ ምልክትና ምስክር ይሆናሉ፤ በዚያ የሚኖሩ ሕዝቦች ችግር ሲደርስባቸው እግዚአብሔር እንዲረዳቸው በሚጠይቁበት ጊዜ የሚታደጋቸውን አዳኝ ይልክላቸዋል፤ እርሱም ከጠላቶቻቸው ያድናቸዋል።
ይህም በሚፈጸምበት ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “እነሆ፥ እርሱ አምላካችን ነው፤ በእርሱ ስለ ታመንን አድኖናል፤ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ እኛም በእርሱ ታምነናል፤ እርሱ ስለ ታደገን በደስታ ተሞልተን ሐሴት እናደርጋለን!” ይላሉ።
ጉዳይህን አቅርበህ ገለጻ አድርግ፤ ከብዙ ጊዜ በፊት ይህን የተናገሩ ተሰብስበው ይመካከሩ፤ በጥንት ጊዜ የተናገረው ማነው? እኔ እግዚአብሔር አልነበርኩምን? ከእኔ በቀር ጻድቅና አዳኝ አምላክ የለም።
ነገሥታት አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል። የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቂአለሽ፤ የእኔን ርዳታ ለማግኘት የሚጠባበቁ ከቶ አያፍሩም።”
ጨቋኞችሽ የገዛ ሥጋቸውን እንዲበሉ አደርጋለሁ፤ በወይን ጠጅ እንደሚሰክሩ የገዛ ደማቸውን ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ። ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ የእስራኤል ኀያል አምላክ መሆኔን የዓለም ሕዝብ ሁሉ ያውቃል።”
“እኔ በነሐስ ፈንታ ወርቅ፥ በብረት ፈንታ ብር፥ በእንጨት ፈንታ ነሐስ፥ በድንጋይም ፈንታ ብረት አመጣለሁ፤ ሰላምን እንደ አስተዳዳሪሽ ጽድቅንም እንደ ገዢሽ አድርጌ እመድባለሁ።
እናንተ ግን “የእግዚአብሔር ካህናትና የአምላካችን አገልጋዮች” ተብላችሁ ትጠራላችሁ። በሕዝቦች ሀብት ትደሰታላችሁ፤ በብልጽግናቸውም ትከብራላችሁ።
አብርሃም ባያውቀን፥ እስራኤል ባይቀበለንም እንኳ አንተ አባታችን ነህ፤ አምላክ ሆይ! ስምህ ከጥንት እንደ ሆነ ሁሉ አንተ አባታችን ነህ፤ አንተ ታዳጊአችን ነህ።
ይህም ሲፈጸም በምታዩበት ጊዜ ሐሴት ታደርጋላችሁ፤ ሰውነታችሁም እንደ ሣር ይለመልማል፤ የእግዚአብሔር ኀይል ከአገልጋዮቹ ጋር፥ ቊጣው ግን በሚጠሉት ላይ እንደሚሆን ይታወቃል።”
እነርሱ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር እንደ ሆንኩና እስራኤላውያን የእኔ ሕዝብ መሆናቸውን ያውቃሉ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።