ኢሳይያስ 59:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሸረሪት ድር ልብስ ለመሥራት አይጠቅምም፤ ማንም ለልብስ አይጠቀምበትም፤ ሥራቸው የበደል ሥራ ነው፤ እጆቻቸውም በዐመፅ ሥራ የተሞሉ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድሮቻቸው ልብስ አይሆኑም፤ በሚሠሩትም ሰውነታቸውን መሸፈን አይችሉም፤ ሥራቸው ክፉ ነው፤ እጃቸውም በዐመፅ ሥራ የተሞላ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድሮቻቸውም ልብስ አይሆኑላቸውም፥ ራሳቸውንም በሠሩት መሸፈን አይችሉም፤ ሥራቸውም የበደል ሥራ ነው፥ የግፍም ሥራ በእጃቸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሸረሪቶች ድር ልብስ አይሆንም፤ በሥራቸውም ራሳቸውን አያለብሱም፤ ሥራቸው የግፍ ሥራ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድሮቻቸውም ልብስ አይሆኑላቸውም፥ በሥራቸውም አይሸፈኑም፥ ሥራቸውም የበደል ሥራ ነው፥ የግፍም ሥራ በእጃቸው ነው። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዐመፀኞች ለሆኑ ልጆች ወዮላቸው! እኔ ባላወጣሁላቸው ዕቅድ መመራት ይፈልጋሉ፤ ከእኔም ፈቃድ ውጪ የቃል ኪዳን ውል በመፈጸም በኃጢአት ላይ ኃጢአት ይጨምራሉ።
ይህም የሠራዊት አምላክ የወይን ቦታ የተባለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፤ እርሱም የይሁዳ ሕዝብ ደስ የሚሰኝበት ተክል ነው። መልካም ሥራ እንዲሠሩ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ በዚህ ፈንታ ነፍሰ ገዳዮች ሆኑ፤ ቅን ፍርድ ይሰጣሉ ብሎ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ እነርሱ ግን ፍርድን በማጓደላቸው የሕዝቡ ጩኸት በዛ።
የጾማችሁ መጨረሻው ጠብና ጭቅጭቅ ስለ ሆነ ጭካኔ በተሞላበት ቡጢ ትማታላችሁ፤ እንደዚህ አድርጋችሁ የምትጾሙት ጾም ጸሎታችሁን በላይ በሰማይ እንዲሰማ አያደርገውም።
እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል።
ጒድጓድ ውሃን እንደሚያፈልቅ፥ ኢየሩሳሌምም የክፋት ሁሉ መፍለቂያ ናት፤ በእርስዋ የሚሰማው የግፍና የጥፋት ጩኸት ብቻ ነው፤ ዘወትር የሚታይባትም ሕመምና ቊስል ነው።
ድኾችንና ችግረኞችን ቢያስጨንቅ፥ ቢቀማ፥ ገንዘብ ሲያበድር በመያዣ ስም የወሰደውን ቢያስቀር፥ በአሕዛብ መስገጃ ስፍራዎች ጣዖትን ቢያመልክ አጸያፊ ነገሮችን ቢያደርግ፥
ከዐመፅ የተነሣ ክፉ ሥራ በዝቶአል፤ ከእነርሱ መካከል አንዳቸውም አይተርፉም። ከብልጽግናቸውና ከተትረፈረፈ ሀብታቸው አንድ ነገር እንኳ አይኖርም።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ እጅግ የከፋ ኃጢአት በመሥራት በድለዋል፤ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ግድያ ፈጽመዋል፤ ከተማይቱንም በዐመፅ የተሞላች አድርገዋታል፤ ‘እግዚአብሔር አገራችንን ትቶአታል፤ እኛንም አይመለከተንም’ ይላሉ፤
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል፦ “በሕዝቤ ላይ በጠላትነት ተነሥታችኋል፤ ከጦርነት ተመልሰው በመተማመን በመካከላችሁ የሚያልፉትን ሰላማዊ ሰዎች ገፈፋችሁ፤
በዚያን ቀን በአሕዛብ የአምልኮ ሥርዓት በቤተ መቅደሱ መድረክ ላይ እየዘለሉ የሚያመልኩትንና የጌታቸውን ቤት በዓመፅና በማታለል በተገኙ ዕቃዎች የሚሞሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።”
“እኔ የባልና የሚስትን መፋታት እጠላለሁ፤ ልብስን በፍትሕ አልባነት መሸፈንንም እጠላለሁ ሰውነቱን በልብስ እንደሚሸፍን በግፍ ሥራ የሚሸፍንን ሰው እጠላለሁ፤ ስለዚህ እምነተቢስ ከመሆን ተጠንቀቁ።” ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር።