ኢሳይያስ 59:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ የእባብ ዕንቊላል ይቀፈቅፋሉ፤ የሸረሪት ድርም ይፈትላሉ፤ እነዚያን ዕንቊላሎች የሚበላ ሁሉ ይሞታል፤ ከሚቀፈቀፈው ዕንቊላል እፉኝት ይወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእባብ ዕንቍላል ታቀፉ፤ የሸረሪት ድር ዐደሩ፤ ዕንቍላሎቻቸውን የሚበላ ሁሉ ይሞታል፤ አንዱ በተሰበረ ጊዜም እፉኝት ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእባብን እንቁላል ቀፈቀፉ፥ የሸረሪትንም ድር አደሩ፤ እንቁላላቸውንም የሚበላ ሰው ይሞታል፥ እንቁላሉም ሲሰበር እፉኝት ይወጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእባብን ዕንቍላል ቀፈቀፉ፤ የሸረሪትንም ድር አደሩ፤ እንቁላላቸውንም የሚበላ ሰው ፈጥኖ ይሞታል፤ እንቍላሉም ሲሰበር እባብ ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእባብን እንቍላል ቀፈቀፉ፥ የሸረሪትንም ድር አደሩ፥ እንቍላላቸውንም የሚበላ ሰው ይሞታል፥ እንቍላሉም ሲሰበር እፉኝት ይወጣል። |
የፍልስጥኤም ሕዝብ ሆይ! እነሆ የተደበደባችሁበት በትር ተሰበረ፤ ሆኖም ደስ ሊላችሁ አይገባም፤ አንድ እባብ በሞተ ጊዜ ሌላ ከእርሱ የባሰ በቦታው ይተካል፤ ከእባብ ዕንቊላል በክንፍ የሚበር እሳት የመሰለ ዘንዶ ይፈለፈላል።
በዚያም ጒጒቶች ጎጆ ሠርተው እንቊላል ይጥላሉ፤ እንቁላሎቻቸውንም ፈልፍለው በክንፎቻቸው ጥላ ሥር ይንከባከባሉ፤ አሞራዎችም ከጓደኞቻቸው ጋር በዚያ ይሰባሰባሉ።
ነገር ግን፥ ዮሐንስ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእባብ ልጆች! ከሚመጣው ቊጣ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ?