ኢሳይያስ 54:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ የተሠቃየሽ፥ በዐውሎ ነፋስም የተዋከብሽና ያልተጽናናሽ የኢየሩሳሌም ከተማ! እኔ በከበረ ድንጋይ እሠራሻለሁ፤ መሠረትሽንም የምጥለው በሰንፔር ድንጋይ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንቺ የተጨነቅሽ ከተማ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ የተናወጥሽ፣ ያልተጽናናሽም፤ እነሆ፤ በከበሩ ድንጋዮች አስጊጬ እገነባሻለሁ፤ በሰንፔር ድንጋይም እመሠርትሻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንቺ የተሸገርሽ በአውሎ ነፋስም የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፥ እነሆ፥ ድንጋዮችሽን ሸላልሜ እገነባለሁ፥ በሰንፔርም እመሠርትሻለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንቺ የተቸገርሽ የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፥ እነሆ፥ ድንጋዮችሽን የሚያበሩ አደርጋለሁ፤ መሠረትሽንም የሰንፔር አደርገዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንቺ የተሸገርሽ በዓውሎ ነፋስም የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፥ እነሆ፥ ድንጋዮችሽን ሸላልሜ እገነባለሁ፥ በሰንፔርም እመሠርትሻለሁ። |
የምችለውን ያኽል፥ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሚሆኑትን ዕቃዎች ወርቅ ለወርቅ ሥራ፥ ብር ለብር ሥራ፥ ነሐስ ለነሐስ ሥራ፥ ብረት ለብረት ሥራ፥ እንጨት ለእንጨት ሥራ መርግድና የተለያዩ ቀለማት ያላቸው በፈርጥ የሚገቡ ድንጋዮች፥ የከበረ ድንጋይና በየዐይነቱ ብዙ ዕብነ በረድ አዘጋጅቼአለሁ።
ከብዙ ዓመቶች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ እስራኤላውያን ግን አሁንም በባርነት ቀንበር ሥር በመጨነቅ ርዳታ ለማግኘት በመጮኽ ላይ ነበሩ፤ ጩኸታቸውም ወደ እግዚአብሔር ደረሰ።
እዚያም የእግዚአብሔር መልአክ በቊጥቋጦ ውስጥ በተቀጣጠለ የእሳት ነበልባል መካከል ሆኖ ተገለጠለት፤ ሙሴም ቊጥቋጦው በእሳት ተያይዞ ሳለ ምንም አለመቃጠሉን ተመለከተና፥
ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን ጭንቀት አይቻለሁ፤ በአስጨናቂዎቻቸው ምክንያት የሚጮኹትን ጩኸት ሰምቼአለሁ፤ ጭንቀታቸውንም ዐውቃለሁ።
ከፍልስጥኤም ለሚመጡ መልእክተኞች የምንሰጠው መልስ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደገና መመሥረቱንና በሥቃይ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቡ መጠጊያ አግኝተው በሰላም እንዲኖሩ ማድረጉን እንነግራቸዋለን።
ስለዚህም ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “እነሆ፥ የጸና የመሠረት ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ እርሱም የተመሰከረለት፥ የከበረ የማእዘን ድንጋይ ነው፤ በእርሱም የሚያምን ሁሉ አይናወጥም።
ቂሮስን ‘የመንጋዬ እረኛ ነህ፤ ዕቅዴን ሁሉ ትፈጽማለህ’ እለዋለሁ፤ ኢየሩሳሌምን ‘አንቺ እንደገና ትገነቢአለሽ’ ቤተ መቅደሱን፥ ‘መሠረትህ ይጣላል’ እላቸዋለሁ።”
የመከራውንም ጽዋ ‘አጐንብሺና በጀርባሽ እንራመድብሽ’ ለሚሉና አንቺን ለሚያሠቃዩ ሰዎች በእጃቸው እሰጣለሁ፤ አንቺም እነርሱ ይራመዱብሽ ዘንድ ጀርባሽን እንደ መሬትና እንደ መንገድ አድርገሻል።”
አንቺ በወጣትነት ዕድሜዋ አግብታ በመባረርዋ ልብዋ እንደ ተሰበረ ሴት ነሽ፤” ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክሽ እንደገና ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ ይልሻል፦
“ከዚህ በፊት የተተውሽና የተጠላሽ ሆነሽ ማንም በአንቺ በኩል የማያልፍ የነበረ ቢሆንም እንኳ፥ የዘለዓለም መመኪያና በየትውልዱ ሁሉ መደሰቻ እንድትሆኚ አደርግሻለሁ።
ጠላቶቻችሁ ‘ጽዮን እንደ ተጣለች መቅረትዋ ነው፤ የሚጠነቀቅላትም የለም’ ቢሉም፥ እኔ ጤንነታችሁን እንደገና እመልስላችኋለሁ፤ ቊስላችሁንም እፈውሳለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
“ጠላቶቼ ሁሉ ማንም የሚያጽናናኝ ሰው በሌለበት እንዴት እንደምቃትትና እንደምቸገር ሰሙ፤ አንተ ያደረግኸው መሆኑንም ዐውቀው ተደሰቱ፤ በእነርሱ ላይ ልታመጣባቸው የወሰንከውን ቀን አምጣና እንደ እኔ ይሁኑ።
ይህን ለእናንተ መናገሬ በእኔ ሆናችሁ ሰላም እንዲኖራችሁ ብዬ ነው፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፥ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”
በእነዚያም አገሮች ሁሉ አማኞች በእምነታቸው እንዲጸኑ በማበረታታትና በመምከር “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ብዙ መከራ መቀበል አለብን” እያሉ አስተማሩአቸው።
ይህም በሚሆንበት ጊዜ እኔ በእነርሱ ላይ ተቈጥቼ እለያቸዋለሁ፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይደመሰሳሉ፤ በእነርሱም ላይ ብዙ አሠቃቂ መቅሠፍት ይመጣባቸዋል፤ በዚያን ጊዜ፥ ‘ይህ ችግር የመጣብን አምላካችን በመካከላችን ስለሌለ አይደለምን?’ ይላሉ።