ኢሳይያስ 52:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማንኛውም ሰው በላይ መልኩ በጣም ተጐሳቊሎ ስለ ነበረ ሁናቴውን ያዩ ሰዎች አብዛኞቹ በጣም ደነገጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙዎች በርሱ እስኪደነግጡ ድረስ፣ መልኩ ከማንም ሰው ተለየ፤ ከሰው ልጆችም ሁሉ ይልቅ ተጐሳቈለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቁሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፥ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ያለ ክብር ነውና ብዙ ሰዎች ስለ እርሱ ያደንቃሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቍሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፥ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፥ |
ወደ ኢየሩሳሌም በሚወስደው መንገድ ሳሉ፥ ኢየሱስ እፊት እፊታቸው ይሄድ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱም በዚህ ነገር ተገረሙ፤ በስተኋላ የሚከተሉትም ፈርተው ነበር። እንደገናም ዐሥራ ሁለቱን ወደ እርሱ አቅርቦ፥ ስለሚደርስበት ነገር እንዲህ ሲል ገለጸላቸው፦
ሁሉም በመደነቅ እርስ በርሳቸው፥ “ይህ ምን ዐይነት ቃል ነው? በሥልጣንና በኀይል ርኩሳን መናፍስትን ያዛል፤ እነርሱም ታዘው ይወጣሉ፤” ተባባሉ።