ኢሳይያስ 51:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንቺ ከእግዚአብሔር እጅ የሚያንገዳግደውን የቊጣውን ጽዋ በትልቅ ዋንጫ ጨልጠሽ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ! ንቂ፤ ተነሥተሽም ቁሚ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእግዚአብሔር እጅ፣ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ፣ ዝቃጩ እንኳ ሳይቀር፣ ሰዎችን የሚያንገደግደውን ዋንጫ የጨለጥሽ፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጌታ እጅ የቁጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ! ቁሚ፤ የሚያንገደግድን ዋንጫ ጠጥተሻል ጨልጠሽውማል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔር እጅ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቁሚ፤ የሚያንገደግድሽን የቍጣውን ጽዋ ጠጥተሻልና፥ ጨልጠሽውማልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር እጅ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ፥ ቁሚ፥ የሚያንገደግድን ዋንጫ ጠጥተሻል ጨልጠሽውማል። |
እግዚአብሔር የተቀመመ ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ በእጁ ይዞአል፤ በቊጣው ሲያፈስሰው ክፉዎች ሁሉ ይጠጡታል፤ እስከ መጨረሻው ጠብታ ድረስ ይጨልጡታል።
የባርነት ጊዜዋ እንዳለቀ፥ ለፈጸመችው ኃጢአት ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ እጥፍ ቅጣት እንደ ተቀበለችና ኃጢአትዋም ይቅር እንደ ተባለላት ለኢየሩሳሌም በለሰለሰ አነጋገር ንገሯት።”
የሕዝቡን አቤቱታ የሚመለከተው አምላካችሁ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እንደ ሰከረ ሰው የሚያንገዳግደውን የመከራ ጽዋ ከእጃችሁ ወስጄአለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ኀይለኛ ቊጣዬን ከትልቁ ዋንጫ አትጠጡም።
እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ተነሥተህ ኀይልህን ግለጽ! በጥንት ዘመን በነበረው ትውልድ መካከል እንዳደረግኸው ተነሥ፤ ረዓብ የተባለውን የባሕር ዘንዶ ቈራርጠህ ያደቀቅከው አንተ ነህ።
ጽዮን ሆይ! ተነሺ፤ ንቂ! ኀይልሽን እንደ ልብስ ልበሺ! ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ! የተዋበ ልብስሽን ልበሺ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ያልተገረዙና በሥርዓት ያልነጹ ሰዎች ወደ ቅጥርሽ ውስጥ አይገቡም።
ከዚህ በኋላ እኔ እግዚአብሔር በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ እስከሚሰክሩ ድረስ በወይን ጠጅ ልሞላቸው እንዳቀድኩ ንገራቸው፤ በዚያን ጊዜ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡ ነገሥታትን፥ ካህናትን፥ ነቢያትንና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችን ሁሉ በወይን ጠጅ አሰክራቸዋለሁ።
የኢየሩሳሌምና የይሁዳ ከተሞች ሕዝብ ከነገሥታቱና ከመኳንንቱ ጋር ከዚህ ጽዋ እንዲጠጡ ተደረገ፤ ከዚህም የተነሣ እነዚህ ስፍራዎች ለማየት እጅግ የሚያስፈራ በረሓ መሳደቢያና መራገሚያ ቦታዎች ይሆናሉ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ከማመጣው ጦርነት የተነሣ ሰክረው እስከሚያስመልሳቸውና ወድቀውም መነሣት እስኪሳናቸው ድረስ እንዲጠጡ የማዛቸው መሆኔን ለሕዝቡ ንገር፤
ስለዚህም በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ቊጣዬንና መዓቴን በማፍሰስ በእሳት እንዲጋዩ አደረግሁ፤ እነርሱም ዛሬ እንደሚታዩት ሁሉ ፍርስራሾችና ባድማ ሆነዋል።
“ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ላሉ ሕዝቦች ጠጥተውት እንደሚያንገዳግድ የወይን ጠጅ ዋንጫ አደርጋታለሁ፤ እነርሱ ኢየሩሳሌምን በሚይዙ ጊዜ የቀሩትም የይሁዳ ከተሞች ይከበባሉ።
ኢየሱስ ግን “እናንተ የምትለምኑትን አታውቁም፤ እኔ በቅርብ ጊዜ የምጠጣውን የመከራ ጽዋ መጠጣት ትችላላችሁን?” አላቸው። እነርሱም “አዎ እንችላለን!” አሉ።
ወደ ልቡናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአትም አትሥሩ፤ በእናንተ መካከል አንዳንዶች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉ። ይህንንም የምለው እንድታፍሩ ብዬ ነው።
የእግዚአብሔርን የቊጣ የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፤ ይህም የወይን ጠጅ ሳይበረዝ በቊጣው ጽዋ የተቀዳ ነው፤ እንዲሁም በቅዱሳን መላእክት ፊትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሠቃያሉ፤
ታላቂቱ ከተማ ከሦስት ተከፈለች፤ የአሕዛብ ከተሞችም ፈራረሱ፤ እግዚአብሔር ታላቂቱን ባቢሎንን አስታወሰ፤ የብርቱ ቊጣው ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ እንድትጠጣም አደረጋት።
በሰጠችው መጠን ስጥዋት፤ ባደረገችውም ሥራ እጥፍ ክፈልዋት፤ እርስዋ ልዩ ልዩ መጠጦችን በቀላቀለችበት ጽዋ ውስጥ እጥፍ ኀይለኛ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤