ሌሎች አማልክትን የሚያመልኩ ብዙ ሐዘን ይደርስባቸዋል፤ እኔ እንደነዚህ ላሉት አማልክት የደም መሥዋዕትን አላቀርብም፤ እነርሱንም አላመልክም።
ኢሳይያስ 50:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ሁላችሁም ነገር በሰው ላይ እንደ እሳት የምታነዱና እንደ ችቦ የምትለኲሱ ናችሁ፤ ባነደዳችሁት እሳት ነበልባል ውስጥና በለኰሳችሁት ችቦ ትጠፋላችሁ ይህንንም ቅጣት የምትቀበሉት ከእኔ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን ግን እናንተ እሳት አንድዳችሁ፣ የራሳችሁን የሚንቦገቦግ ችቦ የያዛችሁ ሁሉ፣ በሉ በእሳታችሁ ብርሃን ሂዱ፤ ባንቦገቦጋችሁትም የችቦ ብርሃን ተመላለሱ። እንግዲህ ከእጄ የምትቀበሉት ይህ ነው፤ በሥቃይም ትጋደማላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ እሳት የምታነድዱ፥ የእሳትንም ወላፈን የምትታጠቁ ሁላችሁ፥ በእሳታችሁ ነበልባል ባነደዳችሁትም ወላፈን ሂዱ! ይህ ከእጄ ይሆንባችኋል፤ በኅዘን ትተኛላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ እሳት የምታነድዱ፥ የእሳትንም ነበልባል ከፍ ያደረጋችሁ ሁላችሁ፥ በእሳታችሁ ብርሃንና ባነደዳችሁት ነበልባል ሂዱ፤ ስለ እኔ ይህ ይሆንባችኋል፤ በኀዘንም ትተኛላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ እሳት የምታነድዱ የእሳትንም ወላፈን የምትታጠቁ ሁላችሁ፥ በእሳታችሁ ነበልባል ባነደዳችሁትም ወላፈን ሂዱ፥ ይህ ከእጄ ይሆንባችኋል፥ በኅዘን ትተኛላችሁ። |
ሌሎች አማልክትን የሚያመልኩ ብዙ ሐዘን ይደርስባቸዋል፤ እኔ እንደነዚህ ላሉት አማልክት የደም መሥዋዕትን አላቀርብም፤ እነርሱንም አላመልክም።
ለማይጠቅም ምግብ ገንዘባችሁን ለምን ታወጣላችሁ? ለማያጠግብ ነገር ጒልበታችሁን ለምን ታባክናላችሁ? አሁንም በጥንቃቄ አድምጡኝና መልካም የሆነውን ምግብ ብሉ፤ በምርጥ ምግብም ራሳችሁን አስደስቱ።
የሕዝቡ ክፋት ኲርንችቱንና እሾኹን እንደሚያቃጥል እሳት ነው፤ እንደ በረሓ እሳት ደኑን በሚያቃጥልበት ጊዜ ጢሱ ተትጐልጒሎ ሲወጣ ቀጥ ብሎ የቆመ ዐምድ ይመስላል።
ቊጣዬ እንደ እሳት እንዲቀጣጠል ስላደረጋችሁ እርሱም ለዘለዓለም ስለሚነድ የሰጠኋችሁን ርስት ሁሉ እንድታጡና በማታውቁት አገር ጠላቶቻችሁን እንድታገለግሉ አደርጋለሁ።”
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር ስለ እናንተ እንዲህ ይላል፦ “አሁንም ሆነ ወደፊት የማታዳምጡኝ ከሆነ እያንዳንዳችሁ ሄዳችሁ ጣዖቶቻችሁን አምልኩ! ቅዱስ ስሜን ግን ከእንግዲህ ወዲያ በጣዖቶቻችሁና በመባዎቻችሁ እንድታስነውሩት አልፈቅድም።
“በግብጽ ምድር የላክሁትን ዐይነት መቅሠፍት ላክሁባችሁ፤ ጐልማሶቻችሁ በሰይፍ እንዲሞቱ፥ ፈረሶቻችሁም እንዲማረኩ አደረግሁ፤ በሰፈራችሁ በሞቱ ሰዎች የበድን ግማት አፍንጫችሁን ሞላሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።
“ሰብላችሁን የሚያደርቅ ብርቱ ነፋስ ላክሁባችሁ፤ አትክልታችሁንና የወይን ተክላችሁን የበለስና የወይራ ዛፋችሁን ሁሉ አንበጣ በላው፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።
ምላስም እንደ እሳት ናት፤ ምላስ በአካል ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ ክፉ ዓለም ናት፤ አካላችንን ትበክላለች፤ ከገሃነም እንደሚወጣ እሳትም የኑሮአችንን ሂደት ሁሉ ታቃጥላለች።
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ብዙ ተአምራት ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ፤ እርሱ የአውሬው ምልክት የነበረባቸውንና ለአውሬውም ምስል ይሰግዱ የነበሩትን ተአምራት እያደረገ ያስታቸው ነበር፤ እነዚህ ሁለቱ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ከነሕይወታቸው ተጣሉ።