La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 48:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ ጠርቼዋለሁም፤ እኔ አመጣዋለሁ፤ የእርሱም ተልእኮ የተሳካ ይሆናል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔ፣ እኔው ራሴ ተናግሬአለሁ፤ በርግጥ እኔ ጠርቼዋለሁ፤ አመጣዋለሁ፤ ሥራውም ይከናወንለታል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔ እራሴ ተናግሬአለሁ፤ እኔ ጠርቼዋለሁ፤ አምጥቼዋለሁ፥ መንገዱም ትከናወንለታለች።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔ ራሴ ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ እኔ ጠር​ቼ​ዋ​ለሁ፤ አም​ጥ​ቼ​ዋ​ለሁ፤ መን​ገ​ዱም ትከ​ና​ወ​ን​ለ​ታ​ለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔ እራሴ ተናግሬአለሁ፥ እኔ ጠርቼዋለሁ፥ አምጥቼዋለሁ፥ መንገዱም ትከናወንለታለች።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 48:15
8 Referencias Cruzadas  

ስለ እውነትና ስለ ፍትሕ ግርማን ተጐናጽፈህ ድል ለማድረግ ገሥግሥ፤ ኀይልህም ታላላቅ ድሎችን ያስገኛል።


“ድል አድራጊውን አነሣሥቶ ከምሥራቅ ያመጣ፥ እንዲያገለግለው የጠራው ማነው? ሕዝቦችን አሳልፎ ለእርሱ ይሰጣቸዋል። ነገሥታትንም ያስገዛለታል፤ በሰይፉ እንደ ትቢያ በፍላጻዎቹም እንደ ገለባ ይበታትናቸዋል።


ቂሮስን ‘የመንጋዬ እረኛ ነህ፤ ዕቅዴን ሁሉ ትፈጽማለህ’ እለዋለሁ፤ ኢየሩሳሌምን ‘አንቺ እንደገና ትገነቢአለሽ’ ቤተ መቅደሱን፥ ‘መሠረትህ ይጣላል’ እላቸዋለሁ።”


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ቂሮስን ለጽድቅ ሥራ አነሣሥቼዋለሁ፤ መንገዱንም አቀናለታለሁ፤ ከተማዬን ኢየሩሳሌምን እንደገና ይሠራታል፤ በስደት ላይ ያሉ ሕዝቤንም ነጻ ያወጣል፤ ይህንንም የሚያደርገው ማንም ገንዘብ እንዲከፍለው ወይም ውለታውን እንዲመልስለት አይደለም።” የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሮአል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በምራታይምና በፈቆድ ሕዝብ ላይ አደጋ ጣሉ፤ ግደሉ፤ አጥፉአቸውም፤ እኔ የማዛችሁን ሁሉ አድርጉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


ይህም በሆነ ጊዜ ንጉሡ ኢኮንያን ከተማረከ አምስት ዓመት ከአምስት ቀን ሆኖት ነበር፤


ይህን የሕግ መጽሐፍ ምን ጊዜም ከማንበብ አትቈጠብ፤ በእርሱ የተጻፈውን ሁሉ መፈጸም ትችል ዘንድ እርሱን ሌሊትና ቀን አሰላስለው፤ ይህንን ብታደርግ፥ ሁሉ ነገር በተቃና ሁኔታ ይሳካልሃል።