ኢሳይያስ 47:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነሆ፥ እነርሱ እንደ ገለባ እሳት ይበላቸዋል፤ ከነበልባሉ ኀይል ራሳቸውን ሊያድኑ አይችሉም፤ ገለባውም ራስን ለማሞቅ ፍም አይኖረውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፣ እነርሱ ገለባ ናቸው፤ እሳት ይበላቸዋል፤ ከነበልባሉ ወላፈን የተነሣ፣ ራሳቸውን ማዳን አይችሉም። ሰው የሚሞቀው ፍም አይኖርም፤ ተቀምጠው የሚሞቁትም እሳት የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ እንደ እብቅ ይሆናሉ፥ እሳትም ያቃጥላቸዋል ሰውነታቸውንም ከነበልባል ኃይል አያድኑም፤ እርሱም ሰው እንደሚሞቀው ፍም፥ ወይም በፊቱ ሰው እንደሚቀመጥበት እሳት ዓይነት አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ሁሉም እንደ እብቅ እሳት ይቃጠላሉ፤ ሰውነታቸውንም ከነበልባል ኀይል አያድኑም፤ እንደ እሳትም ፍም ይሆኑብሻል፤ በላያቸውም ትቀመጫለሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ እንደ እብቅ ይሆናሉ፥ እሳትም ያቃጥላቸዋል ሰውነታቸውንም ከነበልባል ኃይል አያድኑም፥ እርሱም ሰው እንደሚሞቀው ፊም፥ ወይም በፊቱ ሰው እንደሚቀመጥበት እሳት ያለ አይደለም። |
የእስራኤል ብርሃን እግዚአብሔር ራሱ እሳት ይሆንባቸዋል፤ የእስራኤልም ቅዱስ አምላክ ራሱ በአንዲት ቀን ኲርንችቱንና እሾኹን ሳያስቀር ሁሉን በልቶ እንደሚጨርስ የእሳት ነበልባል ይሆናል።
ከተሰባበረ በኋላ ለእሳት መጫሪያ ወይም ለውሃ መጥለቂያ የሚሆን ከፍ ያለ ገል እንኳ ከመካከሉ እንደማይገኝበት ተንኰታኲቶ እንደሚወድቅ የሸክላ ዕቃ ትሆናላችሁ።”
በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ይፈራሉ፤ ከሐዲዎችም ይርበደበዳሉ፤ ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳትና ከዘለዓለማዊ ነበልባል ጋር ለመኖር የሚችል ማነው ይላሉ።
እነርሱ ገና እንደ በቀለና ሥር እንዳልሰደደ አዲስ ተክል ናቸው፤ እግዚአብሔር ነፋሱን ሲልክ ወዲያውኑ ይደርቃሉ፤ እንደ ገለባም በነው ይጠፋሉ።
“ድል አድራጊውን አነሣሥቶ ከምሥራቅ ያመጣ፥ እንዲያገለግለው የጠራው ማነው? ሕዝቦችን አሳልፎ ለእርሱ ይሰጣቸዋል። ነገሥታትንም ያስገዛለታል፤ በሰይፉ እንደ ትቢያ በፍላጻዎቹም እንደ ገለባ ይበታትናቸዋል።
ግማሹን እሳት አንድዶ ምግቡን ያዘጋጅበታል፤ ሥጋም ጠብሶ እስከሚጠግብ ይመገባል፤ ከሞቀውም በኋላ “ግሩም እሳት ነው! እንዴት ይሞቃል!” ይላል።
የእስራኤል ቅዱስ የሠራዊት አምላክ ያዘዘውን ሕግና ያስተማረውን ሥርዓት ስለ አቃለሉ ገለባና ድርቆሽ በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ የእነርሱም ሥር መሠረት በስብሶ ይጠፋል፤ አበባቸውም ደርቆ እንደ ትቢያ ይበናል።
የባቢሎን ወታደሮች ጦርነቱን አቁመው በምሽጋቸው ተቀመጡ፤ የጀግንነትን ወኔ አጥተው እንደ ሴቶች ሆኑ፤ የከተማይቱ የቅጽር በሮች መወርወሪያዎች ተሰባብረዋል፤ ቤቶችም በእሳት ተቃጥለዋል።
ሰፊው የባቢሎን ቅጽር ወድቆ ከመሬት ይደባለቃል፤ ከፍ ብለው የተሠሩ የቅጽር በሮችዋ በእሳት ይጋያሉ። የሕዝብዋ ድካም ከንቱ ይሆናል፤ ሕዝቦች የደከሙበት ነገር ሁሉ በእሳት ይወድማል። እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”
እቈጣቸዋለሁ፤ ምንም እንኳ ለጊዜው ከእሳቱ ቢያመልጡ እሳቱ ግን ይበላቸዋል፤ እነርሱንም በምትቈጣበት ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።
እንደ ሠረገላ ድምፅ እያሰሙ በተራሮች ጫፍ ላይ ይዘላሉ፤ ገለባን እንደሚያቃጥል እሳትም፥ ሁሉን ነገር ያቃጥላሉ፤ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ብርቱ ሠራዊት በሰልፍ ይተማሉ።
የያዕቆብ ልጆች እንደ እሳት፥ የዮሴፍ ልጆች እንደ ነበልባል፥ የዔሳውም ልጆች እንደ ገለባ ይሆናሉ፤ እሳት ገለባን እንደሚያቃጥል የያዕቆብና የዮሴፍ ልጆች የዔሳውን ልጆች ያጠፋሉ። ይህንንም የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።
ከዚህ በኋላ አንድ ብርቱ መልአክ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ የሚያኽል አንድ ድንጋይ አንሥቶ እንዲህ ሲል ወደ ባሕር ወረወረው፤ “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ በኀይል ተገፍታ ትወድቃለች፤ ከእንግዲህ ወዲህም ከቶ አትገኝም፤