ኢሳይያስ 45:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ሁሉ በእኔ በእግዚአብሔር ድልንና ክብርን ያገኛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የእስራኤል ዘር ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፤ ሞገስንም ያገኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ዘር ሁሉ በጌታ ይጸድቃሉ፥ ይመካሉም ይከብራሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፤ ይከብራሉም ይባላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፥ ይመካሉም ይባላል። |
እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩት አመስግኑት! እናንተ የያዕቆብ ዘሮች ሁሉ አክብሩት! እናንተ የእስራኤል ዘሮች ሁሉ በፍርሃት ከፍ ከፍ አድርጉት!
ወደ ሰማይ ትበትናቸዋለህ፤ ነፋስም ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል፤ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በእኔ በእስራኤል ቅዱስም ትመካለህ።
እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከእግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ዘለዓለማዊ ደኅንነት ትድናላችሁ፤ ለዘለዓለምም ኀፍረትና ውርደት ከቶ አይደርስባችሁም።
ጨለማ በሆነ አገር በድብቅ አልተናገርኩም፤ የያዕቆብን ልጆች፦ ‘ቅርጽ በሌለው ቦታ ፈልጉኝ’ አላልኳቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር እውነቱን እናገራለሁ፤ ትክክል የሆነውንም ነገር እገልጣለሁ።
ልጆቻቸው በወገኖች ዘንድ፥ የልጅ ልጆቻቸውም በሕዝቦች ዘንድ የታወቁ ይሆናሉ። የሚያዩአቸው ሁሉ በእኔ በእግዚአብሔር የተባረኩ ዘሮች መሆናቸውን ያውቃሉ።
ሥራቸው ከንቱ አይሆንም፤ የወለዱአቸው ልጆችና የልጅ ልጆቻቸው በእግዚአብሔር የተባረኩ ስለሚሆኑ ልጆቹን የሚወልዱት ጥፋት እንዲደርስባቸው አይደለም።
ለያዕቆብ ልጆችን እሰጠዋለሁ፤ ይሁዳንም የተራሮቼን ርስት ወራሽ አደርገዋለሁ፤ እኔ የመረጥኩት ምድሪቱን ይይዛል፤ አገልጋዮቼም በዚያ ይኖራሉ።
ስለዚህ ተስፋው የተመሠረተው በእምነት ላይ ነበር፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም ዘሮች ሁሉ ከእግዚአብሔር በጸጋ የተሰጠ መሆኑ በዚህ ተረጋግጦአል። ይህም ሕግን ለሚከተሉት ሰዎች ብቻ ሳይሆን እንደ አብርሃም ላመኑ ሁሉ ነው፤ በዚህም መሠረት አብርሃም የሁላችንም አባት ነውና።
ከእናንተም አንዳንዶቻችሁ እንዲሁ ነበራችሁ፤ አሁን ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በአምላካችን መንፈስ ከኃጢአት ታጥባችኋል፤ ለእግዚአብሔር የተለየ ቅዱስ ሕዝብ ሆናችኋል፤ ጸድቃችኋልም።
ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር በሌላ መመካት ከእኔ ይራቅ፤ በዚህም መስቀል ዓለም ከእኔ ተለይቶአል፤ እኔም ከዓለም ተለይቼአለሁ።
እኛ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናመልክና በውጭ በሚታየው ሥርዓት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ የምንመካ ስለ ሆንን በእውነት ተገርዘናል።