‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
ኢሳይያስ 45:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘ጽድቅና ኀይል የሚገኘው ከእግዚአብሔር ብቻ ነው’ ብለው ስለ እኔ ይናገራሉ፤ የሚጠሉኝ ሁሉ ወደ እኔ መጥተው በዕፍረት ላይ ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ እኔም ሲናገሩ፣ ‘ጽድቅና ኀይል፣ በእግዚአብሔር ብቻ ነው’ ይላሉ።” በርሱ ላይ በቍጣ የተነሡ ሁሉ፣ ወደ እርሱ መጥተው ያፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ እኔም፦ በጌታ ዘንድ ብቻ ጽድቅና ኃይል አለ፥ ወደ እርሱም ሰዎች ይመጣሉ፥ በእርሱም ላይ የተቆጡ ሁሉ ያፍራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክብርና ጽድቅ ወደ እርሱ ይመጣሉ፤ ከእግዚአብሔርም የሚርቁ ሁሉ ያፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ እኔም፦ በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ጽድቅና ኃይል አለ፥ ወደ እርሱም ሰዎች ይመጣሉ፥ በእርሱም ላይ የተቆጡ ሁሉ ያፍራሉ። |
‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
እናንተ አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ ከጥንት ዘመናት ጀምሮ አስቀድሜ አልነገርኳችሁምን? ወይስ አልገለጽኩላችሁምን? ለዚህም እናንተ ምስክሮቼ ናቸሁ፤ ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ከእኔ ሌላ መጠጊያ አለት የለም፤ ማንም የለም።”
አንቺን ለማጥፋት የሚሠራ መሣሪያ ዘላቂነት አይኖረውም፤ ለሚከሱሽ ሁሉ በቂ መልስ ይኖርሻል፤ የእኔ አገልጋዮች ርስትና ከእኔ የሚፈረድላቸው ፍርድ ይህ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።
እኔ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክህ ስላከበርኩህ እነሆ፥ የማታውቃቸውን ሕዝቦች ትጠራለህ፤ የማያውቁህም ሕዝቦች ወደ አንተ ይፈጥናሉ።”
የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ስላከበራችሁ ለእርሱ ክብር ሲሉ በተርሴስ መርከቦች መሪነት ልጆቻችሁን ከብራቸውና ከወርቃቸው ጋር ከሩቅ ቦታ ለማምጣት ደሴቶቹ እኔን ይጠባበቃሉ።
እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
ምድር ቡቃያዎችን እንደምታበቅል፥ የአትክልት ቦታም ተክሎችን እንደምታሳድግ፥ ጌታ እግዚአብሔርም ጽድቅና ምስጋና ከሕዝቦች ሁሉ ዘንድ እንዲፈልቁ ያደርጋል።
“እኔ የይሁዳን ሕዝብ ብርቱ አደርጋለሁ፤ የእስራኤልንም ሕዝብ እታደጋለሁ፤ ስለምራራላቸውም ሁሉንም ወደ አገራቸው እመልሳለሁ፤ ከዚህ በፊት ከቶ ጥዬአቸው እንደማላውቅ ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ስለ ሆንኩ ጸሎታቸውን እሰማለሁ።
በዚያን ጊዜ የይሁዳ አለቆች በልባቸው ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አምላካቸው ስለ ሆነ በኢየሩሳሌም የሚኖሩት ሕዝቡ በእርሱ ኀይልን ያገኛሉ’ ይላሉ።
በእነዚያ ቀኖች ዐሥር የሌላ አገር ሰዎች ወደ አንድ አይሁዳዊ ቀርበው የልብሱን ዘርፍ በመያዝ ‘እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለ ሰማን ከእናንተ ጋር እንሂድ’ ይሉታል።”
እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው ጽድቅ አማካይነት እኛ እንዳገኘነው እምነት ያለ የከበረ እምነት ላገኛችሁት፤
አሕዛብ ተቈጡ፤ የአንተም ቊጣ መጣ፤ ሙታን ፍርድ የሚያገኙበት ጊዜም ደረሰ፤ ለአገልጋዮችህ ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚያከብሩት፥ ለታናናሾችና ለታላላቆች፥ ዋጋቸውን የምትሰጥበት ጊዜ ደረሰ፤ ምድርን ያጠፉአትን የምታጠፋበት ጊዜም ደረሰ።”
መንፈስ ቅዱስና ሙሽራይቱ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማም “ና!” ይበል፤ የተጠማም ይምጣ፤ የፈለገም የሕይወትን ውሃ ያለ ምንም ዋጋ በነጻ ይጠጣ።