አምላካችን ሆይ! በእኛ ላይ አደጋ ሊጥሉ በብዛት የመጡትን እነዚህን ሠራዊት ሁሉ መቋቋም ስለማንችል አንተ ራስህ ፍረድባቸው፤ የአንተን ርዳታ ለማግኘት ዐይናችንን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር ሌላ ምንም ማድረግ እንደሚገባን አናውቅም።”
ኢሳይያስ 45:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ ስለሌለ፥ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ያላችሁ ሁሉ ወደ እኔ ተመልሳችሁ ደኅንነትን አግኙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፣ እኔ አምላክ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና፤ ትድኑ ዘንድ ወደ እኔ ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ በምድር ዳርቻ ያላችሁ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ተመለሱ፤ ትድኑማላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ። |
አምላካችን ሆይ! በእኛ ላይ አደጋ ሊጥሉ በብዛት የመጡትን እነዚህን ሠራዊት ሁሉ መቋቋም ስለማንችል አንተ ራስህ ፍረድባቸው፤ የአንተን ርዳታ ለማግኘት ዐይናችንን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር ሌላ ምንም ማድረግ እንደሚገባን አናውቅም።”
ጸሎታችንን ሰምተህ ድልን ታጐናጽፈናለህ፤ እኛንም ለማዳን ብዙ ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህ፤ ሩቅ ከሆነው ባሕር ማዶ ያሉት ሳይቀሩ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ይታመናሉ።
የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በመመለስና በማረፍ ደኅንነትን ታገኛላችሁ፤ ጸጥ በማለትና በመታመን ኀይል ታገኛላችሁ፤ እናንተ ግን እምቢ አላችሁ።
ጣዖቶቻችሁንም አምጡና በሚፈጸምበት ጊዜ እንድናውቀው ወደ ፊት የሚሆነውን ሁሉ እስቲ ይንገሩን፤ ወደፊት ውጤታቸው ምን እንደሚሆን አስተውለን እንረዳ ዘንድ የቀድሞዎቹ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ይንገሩን፤ ወይም ወደፊት ምን እንደሚከሠት ያስረዱን።
“ወንዶች ልጆቼ ከሩቅ አገር እንዲመጡ በሰሜን በኩል ያሉትን አገሮች ተዉአቸው፥ በደቡብ በኩል ያሉትን አገሮች ‘አትያዙአቸውም’ ብዬ አዛለሁ።
ጉዳይህን አቅርበህ ገለጻ አድርግ፤ ከብዙ ጊዜ በፊት ይህን የተናገሩ ተሰብስበው ይመካከሩ፤ በጥንት ጊዜ የተናገረው ማነው? እኔ እግዚአብሔር አልነበርኩምን? ከእኔ በቀር ጻድቅና አዳኝ አምላክ የለም።
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የያዕቆብን ነገዶች ክብር እንደገና ለማንሣትና የተረፉትን እስራኤላውያን ለመመለስ አገልጋዬ ሆነህ መሥራት ብቻ አይበቃም። ከዚህ የበለጠ ግን አዳኝነቴ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርስ ዘንድ አንተ ለሕዝቦች ሁሉ ብርሃን እንድትሆን አደርግሃለሁ።” ይላል።
እኔ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክህ ስላከበርኩህ እነሆ፥ የማታውቃቸውን ሕዝቦች ትጠራለህ፤ የማያውቁህም ሕዝቦች ወደ አንተ ይፈጥናሉ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ አምላካችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም፤ አዳኛችሁም እኔ ብቻ ነኝ።
እርሱ በእግዚአብሔር ኀይል ተነሥቶ የበግ መንጋውን ያሰማራል፤ ይህንንም የሚያደርገው በግርማዊው በእግዚአብሔር በአምላኩ ስም ነው፤ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ስለሚሆን እነርሱ ያለ ስጋት ይኖራሉ።
“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው።
አዎ! የአባቴ ፈቃድ ወልድን የሚያይና በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲያገኝ ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን ከሞት አስነሣዋለሁ።”
የምንሮጠውም የእምነታችን መሥራችና ፈጻሚ የሆነውን ኢየሱስን በመመልከት ነው፤ እርሱ በፊቱ በተደቀነው ደስታ ምክንያት በመስቀል ላይ የመሞትን ውርደት ከምንም ሳይቈጥር የመስቀልን መከራና ሞት ታገሠ፤ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝም ተቀመጠ።
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው ጽድቅ አማካይነት እኛ እንዳገኘነው እምነት ያለ የከበረ እምነት ላገኛችሁት፤