ይህም ድርጊት እግዚአብሔርን አስቈጣ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ወደ አሜስያስ አንድ ነቢይ ላከ፤ ይህም ነቢይ አሜስያስን “የገዛ ሕዝባቸውን ከአንተ እጅ ለማዳን እንኳ ላልቻሉ ለባዕዳን አማልክት ስለምን ሰገድክ?” ሲል ጠየቀው።
ኢሳይያስ 45:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከየሀገሩ ከስደት ተርፋችሁ የተመለሳችሁ፥ ተሰብስባችሁ በአንድነት ቅረቡ! የእንጨት ጣዖቶችን ይዘው የሚዘዋወሩና ማዳን ወደማይችል ጣዖት የሚጸልዩ ዕውቀት የሌላቸው ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በአንድነት ተሰብሰቡ፤ ቅረቡም፤ እናንተ ከአሕዛብ የኰበለላችሁ፣ ኑ። የዕንጨት ጣዖት የሚሸከሙ፣ ማዳን ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ፣ ዕውቀት የላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ፤ በአንድነትም ተማከሩ፤ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ ዕውቀት የላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፥ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም። |
ይህም ድርጊት እግዚአብሔርን አስቈጣ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ወደ አሜስያስ አንድ ነቢይ ላከ፤ ይህም ነቢይ አሜስያስን “የገዛ ሕዝባቸውን ከአንተ እጅ ለማዳን እንኳ ላልቻሉ ለባዕዳን አማልክት ስለምን ሰገድክ?” ሲል ጠየቀው።
አካዝ ድልን ላጐናጸፉአቸው ለሶርያውያን አማልክት መሥዋዕት አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት “የሶርያ አማልክት የሶርያን ነገሥታት ረድተዋል፤ መሥዋዕት ባቀርብላቸው እኔንም ይረዱኛል” ብሎ በማሰብ ነው፤ ይህም ድርጊት በራሱና በሀገሩ ላይ ጥፋትን አመጣ፤
በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር በምድሪቱ ያለውን የተክልና የዛፍ ቅርንጫፍ ልምላሜ የተዋበና የተከበረ ያደርገዋል፤ ከእስራኤል ወገን ከጥፋት የተረፉት ሁሉ ምድሪቱ በምታስገኘው ሰብል ደስታና ኲራት ይሰማቸዋል።
ሕዝቦች ሁሉ በአንድነት ይሰብሰቡ፤ ከእነርሱ መካከል የአሁንና የቀድሞዎቹን ነገሮች አስቀድሞ የተናገረና የገለጠ ማነው? እውነተኛነታቸውን ለማረጋገጥ ምስክሮቻቸውን ያምጡ። እነርሱም ሰምተው እውነት ነው ይበሉ።
“ቤልና ኔቦ የተባሉት የሐሰት አማልክት ያጐነብሳሉ፤ ጣዖቶቻቸው በጭነት እንስሶች ላይ ተጭነዋል፤ የተጫኑት ምስሎች ለደካማ እንስሳ ከባዶች ናቸው።
“ሁላችሁም ተሰብስባችሁ ኑና አድምጡ! ስለ እነዚህ ነገሮች አስቀድሞ የተናገረ ከጣዖቶች መካከል የትኛው ነው? የእግዚአብሔር ተመራጭ በባቢሎን ላይ ዓላማውን ይፈጽማል። ኀይሉም በባቢሎናውያን ላይ ይሆናል።
ርዳታ ለማግኘት በምትጮኹበት ጊዜ እስቲ የሰበሰባችኋቸው ጣዖቶቻችሁ ያድኑአችሁ! እነርሱን የነፋስ ሽውታ ያስወግዳቸዋል፤ እስትንፋስም ይወስዳቸዋል፤ በእኔ የሚተማመን ግን ምድሪቱ የእርሱ ትሆናለች፤ የተቀደሰ ተራራዬንም ርስት ያደርጋል።”
እንደነዚህ ያሉት ምስሎች በዱባ ተክል ውስጥ ለወፍ ማስፈራሪያ እንደሚተከሉ ነገሮች ናቸው፤ መናገር አይችሉም፤ መራመድ ስለማይችሉ ሰዎች ይሸከሙአቸዋል፤ ጒዳት ማድረስም ሆነ ጥቅም ማስገኘት ስለማይችሉ፥ ፈጽሞ አትፍሩአቸው።”
“የባቢሎን ምርኮኞችና በባቢሎን የነበሩ ስደተኞች ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። አምላካችን እግዚአብሔር በባቢሎናውያን ላይ ስለሚበቀለው በቀል የሚናገሩትን አድምጡ።”
እናንተ ከእስራኤል ማኅበረሰብ ግንኙነት የሌላችሁ፥ ለተስፋው ቃል ኪዳን እንግዶች የሆናችሁ፥ በዚህ ዓለምም አንዳች ተስፋ የሌላችሁ፥ ያለ እግዚአብሔር የምትኖሩ፥ ከክርስቶስም የተለያችሁ እንደ ነበራችሁ አስታውሱ።