ከእናንተ መካከል የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆነ ሁሉ፥ አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፤ በይሁዳ ወደሚገኘው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣና የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ይሥራ።
ኢሳይያስ 45:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ቂሮስን ለጽድቅ ሥራ አነሣሥቼዋለሁ፤ መንገዱንም አቀናለታለሁ፤ ከተማዬን ኢየሩሳሌምን እንደገና ይሠራታል፤ በስደት ላይ ያሉ ሕዝቤንም ነጻ ያወጣል፤ ይህንንም የሚያደርገው ማንም ገንዘብ እንዲከፍለው ወይም ውለታውን እንዲመልስለት አይደለም።” የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሮአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቂሮስን በጽድቅ አስነሥቻለሁ፤ መንገዱን ሁሉ አስተካክዬለታለሁ፤ ከተማዬን እንደ ገና ይሠራታል፤ ምርኮኞቼን ያለ ክፍያ ወይም ያለ ዋጋ፣ ነጻ ያወጣል፤’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ፤ እርሱ ከተማዬን ይሠራል፥ በዋጋም ወይም በደመወዝ ሳይሆን ምርኮኞቼን ያወጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ቂሮስን በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ፤ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ፤ እርሱ ከተማዬን ይሠራል፤ በዋጋም ወይም በጉቦ ሳይሆን ምርኮኞችን ያወጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ፥ እርሱ ከተማዬን ይሠራል፥ በዋጋም ወይም በደመወዝ ሳይሆን ምርኮኞቼን ያወጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። |
ከእናንተ መካከል የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆነ ሁሉ፥ አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፤ በይሁዳ ወደሚገኘው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣና የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ይሥራ።
ጸሎታችንን ሰምተህ ድልን ታጐናጽፈናለህ፤ እኛንም ለማዳን ብዙ ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህ፤ ሩቅ ከሆነው ባሕር ማዶ ያሉት ሳይቀሩ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ይታመናሉ።
ከተሞችን ደምስሶ ዓለምን ወደ ምድረ በዳነት የለወጣት ሰው ይህ ነውን? እስረኞች ነጻ እንዳይለቀቁና ወደ ቤታቸው እንዳይገቡ የሚያደርግ እርሱ አልነበረምን?”
“ድል አድራጊውን አነሣሥቶ ከምሥራቅ ያመጣ፥ እንዲያገለግለው የጠራው ማነው? ሕዝቦችን አሳልፎ ለእርሱ ይሰጣቸዋል። ነገሥታትንም ያስገዛለታል፤ በሰይፉ እንደ ትቢያ በፍላጻዎቹም እንደ ገለባ ይበታትናቸዋል።
“እኔ እግዚአብሔር አንድ መሪ ከሰሜን አስነሥቼአለሁ፤ መጥቶአልም። እርሱም ስሜን የሚጠራና ከፀሐይ መውጫ በኩል የሚመጣ ነው። ሸክላ ሠሪ የሸክላውን ዐፈር እንደሚረግጥ መሪዎችን ይረግጣል።
ቂሮስን ‘የመንጋዬ እረኛ ነህ፤ ዕቅዴን ሁሉ ትፈጽማለህ’ እለዋለሁ፤ ኢየሩሳሌምን ‘አንቺ እንደገና ትገነቢአለሽ’ ቤተ መቅደሱን፥ ‘መሠረትህ ይጣላል’ እላቸዋለሁ።”
ከወደ ምሥራቅ እንደ ነጣቂ ጭልፊት ያለውን እጠራለሁ፤ እርሱም ዓላማዬን የሚፈጽም፥ ከሩቅ አገር የሚመጣ ሰው ነው፤ የተናገርኩትን አደርጋለሁ፤ ያቀድኩትንም እፈጽማለሁ።
እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፦ “አንቺን የሚቃወሙሽን እኔ ስለምቃወም፥ ጀግና የያዘው ምርኮኛ እንኳ ይወሰዳል፤ ከጨካኝ እጅም ምርኮ ይለቀቃል፤ እኔም ልጆችሽን አድናለሁ።
የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት እየቃተታችሁ ተንፈራፈሩ፤ ከከተማ ተባራችሁ በሜዳ ላይ ትሰፍራላችሁ ወደ ባቢሎንም ትሄዳላችሁ፤ ይሁን እንጂ በዚያ እግዚአብሔር ያድናችኋል፤ ከጠላቶቻችሁም እጅ ይታደጋችኋል።