ኢሳይያስ 43:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ወንዶች ልጆቼ ከሩቅ አገር እንዲመጡ በሰሜን በኩል ያሉትን አገሮች ተዉአቸው፥ በደቡብ በኩል ያሉትን አገሮች ‘አትያዙአቸውም’ ብዬ አዛለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሜንን፣ ‘አምጣ!’ ደቡብንም፣ ‘ልቀቅ’ እላለሁ፤ ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሜንን፦ “መልሰህ አምጣ፥” ደቡብንም፦ “ልቀቅ፥ ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፥ አምጣ እለዋለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሜንን፦ መልሰህ አምጣ፤ ደቡብምን፦ አትከልክል፤ ወንዶች ልጆችን ከሩቅ፥ ሴቶች ልጆችንም ከምድር ዳርቻ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሜንን፦ መልሰህ አምጣ፥ ደቡብንም፦ አትከልክል፥ ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፥ በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ። |
በዚያን ጊዜ ጌታ በመላው ዓለም ተበታትነው ይኖሩ የነበሩትን የእስራኤልንና የይሁዳን ሕዝብ ከአራቱ ማእዘን ሰብስቦ ያመጣቸው መሆኑን ለመንግሥታት ሁሉ የሚያሳውቅበትን አርማ ከፍ አድርጎ ያቆማል።
የሠራዊት አምላክ በዓለም ሁሉ የመፈራት ግርማ ካላቸው፥ ቆዳቸው ለስላሳ፥ ቁመታቸው ረጅም ኀያላንና ብርቱዎች ከሆኑት፥ በወንዞች የተከፋፈለች ምድር ካላቸው ከእነዚያ ሕዝብ መባ የሚቀበልበት ጊዜ ይመጣል፤ እነርሱም የሠራዊት አምላክ ወደሚመለክባት ወደ ጽዮን ኰረብታ ይመጣሉ።
በዚያም ዘመን ትልቅ መለከት ይነፋል፤ በአሦር ምድር ጠፍተው የነበሩትና ወደ ግብጽ ተሰደው የነበሩት እስራኤላውያንም ተመልሰው በኢየሩሳሌም በሚገኘው በተቀደሰው ተራራ ላይ ይሰግዳሉ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወንዶች ልጆችሽን በክንዳቸው፥ ሴቶች ልጆችሽንም በትከሻቸው ተሸክመው ያመጡ ዘንድ ለመንግሥታት ምልክት እሰጣለሁ፤ ለሕዝቦችም ዐርማን አነሣለሁ።
ቀና ብለሽ በዙሪያሽ ያለውን ሁኔታ ተመልከቺ! ሁላቸውም ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽም በሞግዚቶቻቸው ክንድ ሆነው ወደ አንቺ ይመጣሉ።
የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ስላከበራችሁ ለእርሱ ክብር ሲሉ በተርሴስ መርከቦች መሪነት ልጆቻችሁን ከብራቸውና ከወርቃቸው ጋር ከሩቅ ቦታ ለማምጣት ደሴቶቹ እኔን ይጠባበቃሉ።
ወንድሞቻችሁን ሁሉ ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቅዱስ ተራራዬ በፈረሶች፥ በሠረገሎች፥ በጋሪዎች፥ በበቅሎዎችና በግመሎች አድርገው ከተለያዩ አገሮች ለእግዚአብሔር እንደ መባ ያመጡአቸዋል፤ እነርሱንም የሚያመጡአቸው እስራኤላውያን የእህል ቊርባንን በሥርዓት በነጻ ዕቃ ለእኔ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሚያቀርቡ አድርገው ነው፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
በዚህ ፈንታ፥ የእስራኤልን ሕዝብ ከሰሜን ምድርና ተበታትነው ከነበሩባቸው ሌሎች አገሮች ሰብስቤ ባመጣኋቸው በእኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም ይምላሉ፤ ከዚያም በኋላ በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ።”
በእርግጥ እላችኋለሁ ታገኙኛላችሁ፤ እኔም ወደ ምድራችሁ እመልሳችኋለሁ፤ እናንተን ከበተንኩበት ከየትኛውም አገርና ከየትኛውም ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ እኔ እናንተን ነቅዬ እንድትሰደዱ ከማድረጌ በፊት ወደ ነበራችሁበት ምድር መልሼ አመጣችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
“እናንተ እምነት የማይጣልባችሁ ሕዝብ ሆይ! የእኔ ስለ ሆናችሁ ተመለሱ፤ ከእናንተ መካከል ከየአንዳንዱ ከተማ አንዳንድ፥ ከእያንዳንዱም ቤተሰብ ሁለት ሁለት መርጬ ወደ ጽዮን ተራራ አመጣችኋለሁ።
“እኔ ከሰሜን አመጣቸዋለሁ፤ ከምድር ዳርቻም እሰበስባቸዋለሁ፤ ዕውሮች፤ አንካሶች፥ ነፍሰጡሮችና በምጥ የተያዙ ሴቶች ሁሉ ከእነርሱ ጋር አብረው ይመጣሉ፤ ታላቅ ሕዝብ ሆነው ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፤
እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕዝቤን ሁሉ ከተበተኑባቸው ሕዝቦች መካከል በአንድነት ሰብስቤ ወደገዛ ምድራቸው መልሼ የማመጣቸው መሆኔን ንገራቸው።
እነሆ አሁን ከተሸጡባቸው ስፍራዎች አነሣሥቼ እንዲወጡ አደርጋለሁ፤ በእነርሱ ላይ የፈጸማችሁትን በደል ሁሉ በእናንተ ላይ መልሼ አመጣባችኋለሁ።
በጥቋቊር ፈረሶች ይሳብ የነበረው ሠረገላ ወደ ሰሜን፥ በነጫጭ ፈረሶች ይሳብ የነበረው ወደ ምዕራብ፥ በቡራቡሬ ፈረሶች ይሳብ የነበረው ወደ ደቡብ አገሮች ይሄዱ ነበር።