ኢሳይያስ 43:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ወደፊት የሚሆነውን ነገር አስቀድሜ ተናግሬአለሁ፤ እናንተን ያዳንኩ እኔ ነኝ፤ ከባዕዳን አማልክት አንድ እንኳ ይህን አላደረገም፤ ለዚህ ሁሉ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገልጫለሁ፤ አድኛለሁ፤ ተናግሬአለሁ፤ በመካከላችሁ እኔ እንጂ ባዕድ አምላክ አልነበረም። እኔ አምላክ እንደ ሆንሁ፣ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተናግሬአለሁ፥ አድኛለሁ፥ አሳይቻለሁ፥ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም፤ ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተናግሬአለሁ፤ አድኜማለሁ፤ መክሬማለሁ፤ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምልኮ አልነበረም፤ ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ሆንሁ እናንተ ራሳችሁ ምስክሮች ናችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተናግሬአለሁ አድኜማለሁ አሳይቼማለሁ፥ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም፥ ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እኔም አምላክ ነኝ። |
“እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ተረድታችሁ ታውቁኝና ታምኑብኝ ዘንድ የመረጥኳችሁ አገልጋዮቼና ምስክሮቼ እናንተ ናችሁ። በእርግጥ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ከእዚህ በፊት አልነበረም፤ ወደ ፊትም አይኖርም።
እናንተ አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ ከጥንት ዘመናት ጀምሮ አስቀድሜ አልነገርኳችሁምን? ወይስ አልገለጽኩላችሁምን? ለዚህም እናንተ ምስክሮቼ ናቸሁ፤ ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ከእኔ ሌላ መጠጊያ አለት የለም፤ ማንም የለም።”
ጨለማ በሆነ አገር በድብቅ አልተናገርኩም፤ የያዕቆብን ልጆች፦ ‘ቅርጽ በሌለው ቦታ ፈልጉኝ’ አላልኳቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር እውነቱን እናገራለሁ፤ ትክክል የሆነውንም ነገር እገልጣለሁ።
“አምላክ እኔ ብቻ መሆኔን ዕወቁ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ የምገድልም፥ ሕይወትንም የምሰጥ እኔ ነኝ፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም ከእጄ ማንም ሊያድን አይችልም