ኢሳይያስ 42:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጣዖቶች ተማምነው ምስሎችን ‘እናንተ አምላኮቻችን ናችሁ’ የሚሉ ኀፍረት ይደርስባቸዋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጣዖት የሚታመኑ ግን፣ ምስሎችን፣ ‘አምላኮቻችን ናችሁ’ የሚሉ፣ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ ፈጽመው ይዋረዳሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተቀረጹትም ምስሎች የሚታመኑ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች፦ “አምላኮቻችን ናችሁ” የሚሉ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ፈጽመውም ያፍራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተቀረጹትም ምስሎች የሚታመኑ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች፥ “አምላኮቻችን ናችሁ” የሚሉ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ ፈጽመውም ያፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተቀረጹትም ምስሎች የሚታመኑ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች፦ አምላኮቻችን ናችሁ የሚሉ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ፈጽመውም ያፍራሉ። |
እርሱም የወርቅ ጒትቻውን ሁሉ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፤ የቀለጠውንም ወርቅ በቅርጽ መሥሪያ ውስጥ አግብቶ የወርቅ ጥጃ አድርጎ ሠራው። እነርሱም “እስራኤል ሆይ! ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን አምላካችን ይህ ነው!” አሉ።
እነርሱ እንዲከተሉት ካዘዝኳቸው መንገድ ወዲያውኑ ወጥተዋል፤ ከቀለጠ ወርቅ ጥጃ ሠርተውም ሰግደውለታል፤ መሥዋዕትም አቅርበውለት ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን አምላካችን ይህ ነው’ ብለዋል።
እነርሱንም የሚያመልኩ ሁሉ ያፍራሉ፤ ጣዖትን የሚሠሩ ሰዎች እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሁሉም ይሰብሰቡና በፊቴ ይቁሙ፤ ሁሉም በፍርሃት ይዋጣሉ፤ ያፍራሉም።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አገልጋዮቼ ይበላሉ፤ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ አገልጋዮቼ ይጠጣሉ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ አገልጋዮቼ ይደሰታሉ፤ እናንተ ግን ኀፍረት ይደርስባችኋል።
“ነገር ግን ይህ የማየው ነገር ምንድን ነው? ከፍርሃት የተነሣ ወደ ኋላ በመመለስ ላይ ናቸው፤ ወታደሮቻቸው ድል ሆኑ፤ በየአቅጣጫው ፍርሀትና ሽብር ስላለ ወደ ኋላ መለስ ብለው ሳያዩም ወደ ፊት ሸሹ።