ኢሳይያስ 42:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለረጅም ጊዜ ታገሥኩ፤ ጸጥ ብዬም ራሴን ገታሁ፤ አሁን ግን ምጥ እንደ ያዛት ሴት ከፍተኛ ድምፅ አሰማለሁ፤ የቊጣ እስትንፋስ እተነፍሳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለረዥም ጊዜ ዝም አልሁ፤ ጸጥ አልሁ፤ ራሴንም ገታሁ፤ አሁን ግን ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ እጮኻለሁ፤ ቍና ቍና እቃትታለሁ፤ እተነፍሳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፥ ዝም ብዬም ታግሻለሁ፤ አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እጮኻለሁ፤ አጠፋለሁ በአንድነትም እጨርሳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፤ እንግዲህ ለዘለዓለም ዝም እላለሁን? አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እታገሣለሁ፤ አጠፋለሁ፤ በአንድነትም እጨርሳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፥ ዝም ብዬም ታግሻለሁ፥ አሁን ምጥ እንደያዛት ሴት እጮኻለሁ፥ አጠፋለሁ በአንድነትም እጨርሳለሁ። |
ይህም ሁሉ ሆኖ እግዚአብሔር ምሕረት ሊያደርግላችሁ ተዘጋጅቶአል፤ እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ስለ ሆነ ሊራራላችሁ ወዶአል፤ ስለዚህ በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።”
“እኔን ባለማስታወስና ስለ እኔ ባለማሰብ ውሸት የተናገራችሁት ማንን ፈርታችሁ ነው? እኔን ያልፈራችሁኝ ለብዙ ጊዜ ዝም ስለልኩና እንዳላየ ስለሆንኩ ነውን?
ምጥ የያዛት ሴት የምታሰማውን ጩኸት የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፤ የመጀመሪያ ልጅዋን የምትወልድ በካር ሴት የምታሰማውን ድምፅ የመሰለ ኡኡታም አዳመጥኩ፤ ይህም ድምፅ ኢየሩሳሌም ትንፋሽ አጥሮአት እጅዋን ዘርግታ “ወዮልኝ! ጠፋሁ! እነሆ ሊገድሉኝ መጡ!” እያለች የምታሰማው ጩኸት ነበር።
እነሆ በአሁኑ ጊዜ ምድራችሁ ፍርስራሽ ሆናለች፤ የሚኖርባትም የለም፤ ምድሪቱ አጸያፊ ሆናለች፤ ሕዝብም ሁሉ እንደ ተረገመች ይቈጥሩአታል፤ እግዚአብሔር የዐመፅና የክፋት ሥራችሁን ሁሉ አይታገሥም።