አንሥተውም በትከሻቸው ይሸከሙታል፤ በአንድ ቦታም ሲያኖሩት በዚያው ይቆማል፤ ካለበት ስፍራም መንቀሳቀስ አይችልም። ማንም ሰው ወደ እርሱ ቢጸልይ መልስ አይሰጠውም፤ ወይም ማንንም ከጥፋት ሊያድን አይችልም።
ኢሳይያስ 41:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዞር ብዬ በተመለከትኩ ጊዜ ማንም አልነበረም፤ ከአማልክትም መካከል ምክር የሚሰጥ አልነበረም፤ ጥያቄም ስጠይቅ ማንም መልስ የሚሰጥ አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተመለከትሁ ማንም አልነበረም፤ ከመካከላቸው አማካሪ የለም፤ ስጠይቅም መልስ የሚሰጥ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብመለከት ማንም አልነበረም፤ ብጠይቃቸውም የሚመልስልኝ አማካሪ በመካከላቸው የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአሕዛብና ከአማልክቶቻቸው የሚናገር የለምና፥ ከየትም እንደ ሆኑ ብጠይቃቸው አይመልሱልኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብመለከት ማንም አልነበረም፥ ብጠይቃቸውም የሚመልስልኝ አማካሪ በመካከላቸው የለም። |
አንሥተውም በትከሻቸው ይሸከሙታል፤ በአንድ ቦታም ሲያኖሩት በዚያው ይቆማል፤ ካለበት ስፍራም መንቀሳቀስ አይችልም። ማንም ሰው ወደ እርሱ ቢጸልይ መልስ አይሰጠውም፤ ወይም ማንንም ከጥፋት ሊያድን አይችልም።
“እኔ በመጣሁ ጊዜ ማንም ሰው አለመኖሩ ለምንድን ነው? በጠራሁም ጊዜ ማንም ሰው መልስ ያልሰጠኝ ለምንድን ነው? እኔ ለመታደግ አልችልምን? ለማዳንስ ኀይል የለኝምን? በተግሣጼ ብቻ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ወደ ምድረ በዳነት እለውጣለሁ፤ ዓሣዎቻቸውም ውሃ ከማጣት የተነሣ ሞተው ይበሰብሳሉ።
ዙሪያዬን በተመለከትኩ ጊዜ የሚረዳ ማንም አልነበረም። ደጋፊ ባለመኖሩ ተደነቅሁ፤ ስለዚህ በኀይለኛ ቊጣዬ አማካይነት እኔው ራሴ ድልን አመጣሁ።
ስለዚህ እናንተ በጠራኋችሁ ጊዜ መልስ ስላልሰጣችሁና በተናገርኩም ጊዜ ስላላዳመጣችሁ ለእኔ መታዘዝን ትታችሁ ክፉ ማድረግን ስለ መረጣችሁ ዕድል ፈንታችሁ ለገዳይ ተንበርክኮ በሰይፍ መገደል ይሆናል።”
ጥበበኞቹም ወደ ንጉሡ ቀረቡ፤ ነገር ግን ጽሑፉን ማንበብም ሆነ ትርጒሙን ለንጉሡ ማስረዳት የቻለ ከእነርሱ መካከል የተገኘ ማንም አልነበረም።