ኢሳይያስ 40:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ለደከሙት ብርታትን ይሰጣል፤ ለዛሉትም ኀይልን ይጨምራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለደከመው ብርታት ይሰጣል፤ ለዛለው ጕልበት ይጨምራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፤ ጉልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለደካሞች ኀይልን ይሰጣል፤ መከራ የሚቀበሉትንም አያሳዝናቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለደካማ ኃይልን ይሰጣል ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። |
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከመቅደሱ በሚገለጥበት ጊዜ እጅግ ያስፈራል፤ እርሱ ለሕዝቡ ብርታትንና ኀይልን ይሰጣል። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።
ደካሞችን በቃል ማጽናትን ዐውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የምሁርን አንደበት ሰጥቶኛል፤ በየማለዳው ከእንቅልፍ ያነቃኛል፤ እንደ ተማሪም አዳምጥ ዘንድ ጆሮዬን ይከፍታል።
የእሳትን ኀይል አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከደካማነት ወደ ብርቱነት ተለወጡ፤ በጦርነት ኀይለኞች ሆኑ፤ የወራሪ ጠላትን ወታደሮች አባረሩ፤
እግዚአብሔር በሌሂ ያለው ጐድጓዳ ቦታ ከፈተለት፤ ከእርሱም ውሃ ወጣ፤ በጠጣም ጊዜ መንፈሱ ተመልሶለት ተጠናከረ፤ ስለዚህም ያ ቦታ “ዐይን ሃቆሬ” የተባለ። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ በሌሂ ይገኛል።