ኢሳይያስ 37:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሦራውያን ባለ ሥልጣን ንጉሡ ላኪሸን ለቆ በአቅራቢያ ወዳለችው ወደ ሊብና ከተማ በመሄድ እዚያ በመዋጋት ላይ መሆኑን ሰማ፤ ስለዚህ ወደዚያ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጦር አዛዡም፣ የአሦር ንጉሥ ለኪሶን ትቶ መሄዱን ሲሰማ ተመለሰ፤ ንጉሡም ልብናን ሲወጋ አገኘው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራፋስቂስም ተመለሰ፤ የአሦርም ንጉሥ ከለኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ስለ ነበር በልብና ከተማ ሲዋጋ አገኘው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሦርም ንጉሥ ከለኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበርና ራፋስቂስ ተመልሶ በልብና ሲዋጋ አገኘው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሦርም ንጉሥ ከለኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበርና ራፋስቂስ ተመልሶ በልብና ሲዋጋ አገኘው። |
ንጉሥ ኢዮራም የቀድሞ አባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ስለ ተወ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኤዶም ከይሁዳ በመገንጠል ነጻ መንግሥት ሆነች፤ በዚሁ ወቅት የሊብና ከተማም በይሁዳ ላይ ዐመፀች፤
ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ አንድ ዓመት ነበር፤ እርሱም በኢየሩሳሌም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ የእናቱም ስም ሐሙጣል ይባል ነበር፤ እርስዋም የሊብናው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።
ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ ከሆነችው ኬብሮን ከግጦሽ መሬትዋ ጋር በተጨማሪ ለካህኑ ለአሮን ዘሮች ከዚህ የሚከተሉት ከተሞች ተመደቡላቸው፤ እነርሱም ሊብና፥ ከግጦሽ መሬትዋ ጋር፥