La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 37:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አምላክ ሆይ! የአሦር ነገሥታት ብዙ መንግሥታትን ማጥፋታቸውንና ምድራቸውንም መደምሰሳቸውን ሰምተናል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እግዚአብሔር ሆይ፤ የአሦር ነገሥታት እውነትም እነዚህን አሕዛብንና ምድራቸውን አጥፍተዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ ሆይ፥ በእውነት የአሦር ነገሥታት ዓለሙን ሁሉ አገሮቻቸውንም አፍርሰዋል፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤቱ፥ በእ​ው​ነት የአ​ሦር ነገ​ሥ​ታት ዓለ​ሙን ሁሉ ሀገ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አቤቱ፥ በእውነት የአሦር ነገሥታት ዓለሙን ሁሉ አገሮቻቸውንም አፍርሰዋል፥

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 37:18
7 Referencias Cruzadas  

የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር ዒዮን፥ አቤልቤትማዕካ፥ ያኖሐ፥ ቄዴሽና ሐጾር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች፥ እንዲሁም የገለዓድን፥ የገሊላንና የንፍታሌምን ግዛቶች በመውረር ሕዝቡን ወደ አሦር ማርኮ የወሰደውም ይኸው ፋቁሔ በነገሠበት ዘመን ነበር።


የአካዝን ጥያቄ በመቀበል ቲግላት ፐሌሴር ዘምቶ ደማስቆን በቊጥጥሩ ሥር አደረገ፤ ንጉሥ ረጺንንም ገደለ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ቂር ተብላ ወደምትጠራው ስፍራ ወሰደው።


የአሦር ንጉሠ ነገሥት በባቢሎን፥ ኩታ፥ ዓዋ፥ ሐማትና ሰፋርዋይም ተብለው በሚጠሩት ከተሞች ይኖሩ የነበሩትን አሕዛብ አምጥቶ ተሰደው በሄዱት በእስራኤላውያን እግር በመተካት በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፤ እነርሱም እነዚህን ከተሞች ወርሰው በዚያ መኖር ጀመሩ።


ይኸውም ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰልምናሶር ድል አድርጎ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም ማርኮ በእስረኛነት ወደ አሦር ወሰዳቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ፥ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ ውስጥ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ እንዲሁም ሌሎቹ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።


ስለዚህ እግዚአብሔር ፑል ወይም ቲግላት ፐሌሴር ተብሎ የሚጠራውን የአሦርን ንጉሠ ነገሥት አነሣሥቶ ምድራቸውን እንዲወር አደረገ፤ በዚህ ዐይነት ቲግላት ፐሌሴር የሮቤልን፥ የጋድንና በምሥራቅ በኩል ያለውን የምናሴን ነገድ እኩሌታ ማርኮ በመውሰድ በሐላሕ፥ በሐቦርና በሃራ እንዲሁም በጎዛን ወንዝ ዳርቻ እንዲኖሩ አደረጋቸው እስከ ዛሬም ድረስ በዚያው ይገኛሉ።


“አንቺን የሚገነቡ ፈጣኖች ናቸው፤ ያወደሙሽ ግን ከአንቺ ርቀው ይሄዳሉ።