ኢሳይያስ 34:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤዶም ጅረቶች ወደ ቅጥራንነት፥ ዐፈሩም ወደ ዲንነት ይለወጣሉ፤ ከዚያም ሀገሪቱ በመላ ትቃጠላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤዶም ምንጮች ሬንጅ፣ ዐፈሯ የሚቃጠል ድኝ፣ ምድሯም የሚንበለበል ዝፍት ይሆናል! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤዶሚያስም ፈሳሾች ዝፍት ሆነው ይለወጣሉ፥ አፈርዋም ዲን ይሆናል፥ መሬትዋም የሚቃጠል ዝፍት ትሆናለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሸለቆዎችዋ ዝፍት ሆነው ይወጣሉ፤ አፈርዋም ዲን ይሆናል፤ መሬቷም በቀንና በሌሊት እንደ ዝፍት ይቃጠላል፤ ለዘለዓለምም አይጠፋም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኤዶሚያስም ፈሳሾች ዝፍት ሆነው ይለወጣሉ፥ አፈርዋም ዲን ይሆናል፥ መሬትዋም የሚቃጠል ዝፍት ትሆናለች። |
ከብዙ ዘመናት በፊት የአሦር ንጉሠ ነገሥት የሚቃጠልበት ቦታ ተዘጋጅቶ ነበር፤ ያም ቦታ ሰፊና ጥልቅ ሆኖ ብዙ እንጨት ተከማችቶበት ነበር፤ እንደ ዲን ጅረት የሚፈሰው የእግዚአብሔር እስትንፋስ እሳቱን ያቀጣጥለዋል።
የቦጽራ ከተማ አስፈሪ ምድረ በዳ ሆና እንደምትቀር እኔ በራሴ ምዬአለሁ፤ ሕዝብ ሁሉ መቀለጃ ያደርጋታል፤ ስሟንም እንደ ርግማን ይቈጥሩታል። በአቅራቢያዋ ያሉ መንደሮች ሁሉ ለዘለዓለም ፍርስራሾች ሆነው ይቀራሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
ምድሪቱም ሁሉ በዲንና በጨው ትሸፈናለች፤ ምንም ነገር አይተከልባትም፤ ምንም ነገር አታበቅልም፤ እግዚአብሔር በኀይለኛ ቊጣው እንደ ደመሰሳቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ጺባዮ ትሆናለች።
በዚሁ ዐይነት ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸው ያሉ ከተሞችም ሴሰኞች ሆኑ፤ ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪም ዝሙት ፈጸሙ። ስለዚህ እነርሱ በዘለዓለም እሳት ለሚቀጡት ምሳሌ ሆነዋል።
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ብዙ ተአምራት ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ፤ እርሱ የአውሬው ምልክት የነበረባቸውንና ለአውሬውም ምስል ይሰግዱ የነበሩትን ተአምራት እያደረገ ያስታቸው ነበር፤ እነዚህ ሁለቱ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ከነሕይወታቸው ተጣሉ።
ነገር ግን ፈሪዎች፥ እምነተ ቢሶች፥ ርኩሶች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ አመንዝሮች፥ አስማተኞች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸታሞች ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲን በሚቃጠለው በእሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”