ኢሳይያስ 33:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድሪቱም ደርቃለች፤ ባድማ ሆናለች፤ የሊባኖስ ደኖች ደርቀዋል፤ ለሙ የሳሮን ሸለቆ ወደ በረሓነት ተለውጦአል፤ በባሳንና በቀርሜሎስ ተራራዎች የሚገኙ ዛፎች ቅጠላቸው ረግፎአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱ አለቀሰች፤ መነመነች፤ ሊባኖስ ዐፈረች፤ ጠወለገች፤ ሳሮን እንደ ዓረባ ምድረ በዳ ሆነች፤ ባሳንና ቀርሜሎስ ቅጠላቸውን አረገፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱ አለቀሰች ከሳችም፤ ሊባኖስ አፈረ ጠወለገም፤ ሳሮን እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ባሳንና ቀርሜሎስ ቅጠላቸውን አረገፉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድር አለቀሰች፤ ሊባኖስ አፈረ፤ ሳሮንም እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ገሊላና ቀርሜሎስ ታወቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድርቱ አለቀሰች ከሳችም፥ ሊባኖስ አፈረ ጠወለገም፥ ሳሮን እንደ ምድረ በዳ ሆነ፥ ባሳንና ቀርሜሎስ ቅጠላቸውን አረገፉ። |
በደን መካከል የሚገኝ ዛፍ በመጥረቢያ ተቈርጦ እንደሚወድቅ እነርሱንም እግዚአብሔር ይቈራርጣቸዋል፤ ምርጥ የሆኑ የሊባኖስ ዛፎችም ተቈርጠው እንደሚወድቁ እነርሱም በኀያሉ አምላክ ተቈርጠው ይወድቃሉ።
የሊባኖስ ዛፎችና ዝግባዎች እንኳ ስለ ወደቀው ንጉሥ ደስታቸውን ይገልጣሉ፤ እርሱ ስለ ተወገደ ከእንግዲህ ወዲህ በእነርሱ ላይ መጥረቢያ የሚያነሣባቸው ሰው አይኖርም።
ከዚያ በኋላ ግን እኔ እግዚአብሔር “የእግዚአብሔር መሠዊያ” ተብላ የምትጠራውን የእስራኤል ከተማ አስጨንቃለሁ፤ እዚያም ሐዘንና የለቅሶ ዋይታ ይሆናል፤ ከተማይቱም በደም እንደ ተሸፈነ መሠዊያ ትሆናለች።
ምድረ በዳዎች በፈኩ አበቦች ይሞላሉ፤ የደስታ መዝሙርም ይዘምራሉ፤ እንደ ሊባኖስ ተራራ ግርማ ያላቸው ይሆናሉ፤ እንደ ቀርሜሎስም ተራራ ወይም እንደ ሻሮን ሸለቆ ክብርን የተጐናጸፉ ይሆናሉ። ሁሉም የእግዚአብሔርን ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።
አገልጋዮችህን ልከህ በጌታ ላይ የስድብ ቃል በመናገር፦ ‘በሠረገሎቼ ብርታት ከፍተኛ የሆኑ የሊባኖስ ተራራዎችን ይዤአለሁ፤ ረጃጅም የሆኑትን የሊባኖስ ዛፎችና የተዋቡ የዝግባ ዛፎችን ቈርጬአለሁ፤ በከፍተኛ ስፍራዎች ላይ ጥቅጥቅ ወዳሉት ደኖች አልፌአለሁ፤
የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ምድራቸው እመልሳለሁ፤ በቀርሜሎስ ተራራና በባሳን አውራጃ የሚበቅለውን ሁሉ ይመገባሉ፤ በኤፍሬምና በገለዓድ ከሚበቅለውም እህል የፈለጉትን ያኽል ይመገባሉ፤
አሞጽ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ሆኖ እንደሚያገሣ አንበሳ የሚያስፈራ ድምፁን ያሰማል፤ ቃሉም ከኢየሩሳሌም ያስተጋባል፤ እረኞች መንጋ የሚያሰማሩበት መስክ ይጠወልጋል፤ በቀርሜሎስ ተራራ የሚገኘውም ልምላሜ ይደርቃል።”
እግዚአብሔር ሆይ! የአንተ መንጋ የሆነውን ሕዝብህን በሥልጣንህ ጠብቅ፤ እነርሱም በለመለመ አትክልት ቦታ መካከል በጫካ ውስጥ ብቻቸውን የሚኖሩ ናቸው፤ እንደ ቀድሞው ዘመን በባሳንና በገለዓድ እንዲመገቡ አድርጋቸው።
በዚያኑ ጊዜ ከተሞቹን ሁሉ ያዝን፤ ያልወሰድነው ምንም ከተማ አልነበረም፤ በዚህም ዐይነት የባሳን ንጉሥ ዖግ በአርጎብ ግዛት ያስተዳድራቸው የነበሩትን ሥልሳ ከተሞች ወሰድን።