ኢሳይያስ 33:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አውራ ጐዳናዎች ባዶ ሆኑ፤ በመንገዶቹ ላይ ተጓዦች የሉም፤ ቃል ኪዳን ፈረሰ፤ የውል ስምምነቶች ተጥሰዋል፤ ከዚህም የተነሣ ምክር የሚሰጠው ሰው አልተገኘም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አውራ ጐዳናዎች ባዶ ናቸው፤ በመንገድ ላይ ሰው የለም፤ ስምምነቱ ፈርሷል፤ መካሪዎቹ ተንቀዋል፤ የሚከበርም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አውራ ጎዳናዎች ባድማ ሆኑ፥ መንገዶችም የሚያልፍባቸው ጠፋ፤ እርሱም ቃል ኪዳንን አፈረሰ ከተሞችንም ናቀ፥ ሰውንም አልተመለከተም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገዶች ባድማ ሆኑ፤ የአሕዛብም መፈራት ቀረ፤ ቃል ኪዳናቸውም ፈረሰ፤ እንደ ሰውም አልተመለከታቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዶች ባድማ ሆኑ፥ ተላላፊም ቀረ፥ እርሱም ቃል ኪዳንን አፈረሰ ከተሞችንም ናቀ ሰውንም አልተመለከተም። |
በዚያ “ቅዱስ ጐዳና” የሚባል መንገድ ይኖራል፤ እርሱም ለእግዚአብሔር ሰዎች ይሆናል፤ ንጹሕ ያልሆነ ሰው በዚያ መንገድ አይሄድም፤ ሞኞችም ሊሄዱበት አይችሉም።
ማንም ሰው በዓላቱን ለማክበር ስለማይመጣ የጽዮን መንገዶች ጭር ይላሉ፤ በሮችዋ ሁሉ ባዶ ናቸው፤ ካህናትዋ ይቃትታሉ ልጃገረዶችዋ በሐዘን ይጨነቃሉ የጽዮንም ዕድል ፈንታ የመረረ ይሆናል።
በመካከላችሁ አደገኞች አራዊትን እልካለሁ፤ እነርሱም ልጆቻችሁን ይገድላሉ፤ ከብቶቻችሁንም ያወድማሉ፤ ከእናንተ ጥቂት ሰዎች ብቻ ስለሚቀሩ ጐዳናዎቻችሁ ሁሉ ሰው አልባ ይሆናሉ።
በዐናት ልጅ በሻምጋርና በያዔል ዘመን፥ የሲራራ ነጋዴዎች በምድሪቱ አያልፉም ነበር፤ መንገደኞችም ተደብቀው በዘወርዋራ መንገድ ይሄዱ ነበር፤
ዳዊትም በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች “ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እስራኤልን ከዚህ አሳፋሪ ውርደት ለሚያድን ሰው ምን ይደረግለታል? ኧረ ለመሆኑ የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት የሚፈታተን ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ነው?” ሲል ጠየቀ።