ኢሳይያስ 33:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ነው! በሰማያትም ይኖራል፤ ለጽዮንም ጽድቅንና ፍትሕን ያጐናጽፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በአርያም ተቀምጧልና ከፍ ከፍ አለ፤ ጽዮንን በጽድቅና በፍትሕ ይሞላታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ፤ ጽዮንን በፍትህና በጽድቅ ሞላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአርያም የሚኖር ቅዱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ይኖራል፤ ጽዮንም ፍርድንና ጽድቅን ተሞላች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ፥ ጽዮንን በፍርድና በጽድቅ ሞላት። |
ከዚህ በኋላ ሙሴና የእስራኤል ሕዝብ ከዚህ የሚከተለውን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፦ “ፈረሱንና ፈረሰኛውን ወደ ባሕር በመጣል፥ ክብር የተሞላው ድል ስለ ተጐናጸፈ፥ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።
ግብጻውያን በእስራኤል ሕዝብ ላይ ታብየው ያን ያኽል አሳፋሪ ድርጊት በመፈጸማቸው ይህን ሁሉ አስደናቂ ነገር ስላደረገ እነሆ፥ እኔም እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ የሚበልጥ መሆኑን አሁን ዐወቅሁ።”
በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦ “እግዚአብሔርን አመስግኑ! ስሙንም አክብሩ! በሕዝቦች መካከል እርሱ ያደረገውን ተናገሩ! ስለ ገናናነቱም መስክሩ!
የሰዎች ኲራት ይጠፋል፤ እብሪት የሞላበት ትዕቢታቸውም ያከትማል፤ ጣዖቶች ሁሉ ይደመሰሳሉ፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ብቻ በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
ይህም ሁሉ ሆኖ እግዚአብሔር ምሕረት ሊያደርግላችሁ ተዘጋጅቶአል፤ እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ስለ ሆነ ሊራራላችሁ ወዶአል፤ ስለዚህ በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።”
ጽዮን ሆይ! ተነሺ፤ ንቂ! ኀይልሽን እንደ ልብስ ልበሺ! ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ! የተዋበ ልብስሽን ልበሺ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ያልተገረዙና በሥርዓት ያልነጹ ሰዎች ወደ ቅጥርሽ ውስጥ አይገቡም።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “የማድንበት ጊዜ ፈጥኖ ስለሚመጣና እኔ የምታደግበትም ጊዜ ስለ ቀረበ ፍትሕን ጠብቁ ትክክለኛውንም ነገር አድርጉ።
ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።
ምድር ቡቃያዎችን እንደምታበቅል፥ የአትክልት ቦታም ተክሎችን እንደምታሳድግ፥ ጌታ እግዚአብሔርም ጽድቅና ምስጋና ከሕዝቦች ሁሉ ዘንድ እንዲፈልቁ ያደርጋል።
በጽዮን ለሚያለቅሱት ሰዎች በዐመድ ፈንታ የአበባ ጒንጒንን፥ በእንባቸው ምትክ የወይራ ዘይትን በኀዘን ፈንታ የደስታ ዘይትን፥ በዛለ መንፈሳቸው ፈንታ የምስጋና መጐናጸፊያን ለማስገኘት ላከኝ። እነርሱም ክብሩን እንዲገልጡ እግዚአብሔር የተከላቸው “የጽድቅ ዋርካዎች” ተብለው ይጠራሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ለእኔ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? የማርፍበትስ ቦታ ምን ዐይነት ነው?
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከዳዊት ዘር መካከል ጻድቅ የሆነውን ለንጉሥነት የምመርጥበት ጊዜ ይመጣል፤ ያም ንጉሥ በጥበብ ያስተዳድራል፤ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ትክክልና ቅን የሆነውን ነገር ያደርጋል።
እርሱ በሚነግሥበት ጊዜ የይሁዳ ሕዝብ ደኅንነት ያገኛል፤ የእስራኤልም ሕዝብ በሰላም ይኖራል፤ እርሱም ‘እግዚአብሔር ጽድቃችን’ ተብሎ ይጠራል።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቡን ወደ አገራቸው በመለስኩ ጊዜ በይሁዳና በከተሞቹ እንደገና ‘አንቺ የእውነት ማደሪያ የሆንሽ ቅድስት ተራራ እግዚአብሔር ይባርክሽ’ ይላሉ።
“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”
እንግዲህ በዚህ ዐይነት እስራኤላውያን ሁሉ ይድናሉ። ስለዚህም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፦ “አዳኝ ከጽዮን ይመጣል፤ ከያዕቆብም ዘር ሁሉ ክፋትን ያስወግዳል፤