ኢሳይያስ 32:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እግዚአብሔር መንፈሱን በእኛ ላይ የሚያፈስበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ምድረ በዳው ለም ይሆናል፤ ለሙም መሬት ብዙ ፍሬ ይሰጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የሚሆነው መንፈስ ከላይ እስኪፈስስልን፣ ምድረ በዳው ለም መሬት፣ ለሙ መሬትም ጫካ እስኪመስል ድረስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንፈስ ከላይ እስኪፈስልን፥ ምድረ በዳውም ፍሬያማ እርሻ እስኪሆን፥ ፍሬያማውም እርሻ ዱር ተብሎ እስኪቈጠር ድረስ ይህ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም፥ መንፈስ ከላይ እስኪመጣላችሁ፥ ምድረ በዳውም ፍሬያማ እርሻ እስኪሆን፥ ፍሬያማውም እርሻ ዱር ተብሎ እስኪቈጠር ድረስ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም፥ መንፈስ ከላይ እስኪፈስስልን፥ ምድረ በዳውም ፍሬያማ እርሻ እስኪሆን፥ ፍሬያማውም እርሻ ዱር ተብሎ እስኪቈጠር ድረስ ይሆናል። |
የሚያቃጥለው አሸዋ ኩሬ ይሆናል፤ ደረቁም ምድር በምንጭ ውሃ ይረሰርሳል፤ የቀበሮዎች መፈንጫ የነበረው ስፍራ ለምለም ሣርና ቄጠማ የሚበቅልበት ይሆናል።
“ለተጠማው ምድር ውሃን እሰጣለሁ፤ በደረቀውም ምድር ጅረቶች እንዲፈስሱ አደርጋለሁ፤ መንፈሴን በልጆችህ ላይ አፈሳለሁ፤ በረከትንም ለልጅ ልጆችህ እሰጣለሁ።
እናንተ ከላይ ያላችሁ ሰማያት! ጽድቅን እንደ ዝናብ አውርዱ፤ ደመናም ያርከፍክፈው፤ ምድር ትከፈት፤ ደኅንነትም ያቈጥቊጥ፤ እኔ እግዚአብሔር የፈጠርኩት ስለ ሆነ ጽድቅም ከእርሱ ጋር ይብቀል።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከእነርሱ ጋር የሚኖረኝ ቃል ኪዳን ይህ ነው፦ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም በእናንተ ላይ ያለው መንፈሴና በአንደበታችሁ ያኖርኩትን ቃሌን ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ አስተምሩ ይላል እግዚአብሔር።”
ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የነበረበትን የቀድሞውን ዘመን ማስታወስ ጀመሩ፤ ከመንጋዎቹ እረኞች ጋር ከባሕር ያወጣቸው እግዚአብሔር የት አለ? ቅዱስ መንፈሱን በውስጣቸው ያሳደረው እግዚአብሔር የት ነው?
እስትንፋሴን በእነርሱ ውስጥ አገባለሁ፤ በሕይወትም እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤ በገዛ ምድራቸውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይህን የተናገርኩና የማደርገውም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው።
ይህንንም የተናገረው በእርሱ የሚያምኑ ስለሚቀበሉት ስለ መንፈስ ቅዱስ ነበር፤ ኢየሱስ ገና ወደ ክብር ስላልወጣ መንፈስ ቅዱስ ገና አልተሰጠም ነበር።