ኢሳይያስ 30:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሁሉ ሆኖ እግዚአብሔር ምሕረት ሊያደርግላችሁ ተዘጋጅቶአል፤ እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ስለ ሆነ ሊራራላችሁ ወዶአል፤ ስለዚህ በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን ምሕረት ሊያደርግላችሁ ይታገሣል፤ ርኅራኄም ሊያሳያችሁ ይነሣል። እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ነውና፣ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁት ብፁዓን ናቸው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም የፍርድ አምላክ ነው፤ ስለ ሆነም ጌታ ይራራላችኋልና ይታገሣል፤ ሊምራችሁም ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችን እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፤ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የፍርድ አምላክ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፥ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፥ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው። |
እግዚአብሔር በፊቱ ሲያልፍ እንዲህ ብሎ ዐወጀ፤ “እኔ እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሐሪ አምላክ ነኝ፤ እኔ ለቊጣ የዘገየሁ፤ ዘለዓለማዊ ፍቅሬና ታማኝነቴ የበዛ ነው፤
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፦ “በቀትር ጊዜ በጸጥታ እንደምታበራ ፀሐይ፥ በመከርም ወራት በሞቃት ሌሊት እንደሚታይ ጤዛ ከሰማያዊ መኖሪያዬ ጸጥ ባለ መንፈስ ቊልቊል እመለከታለሁ።
የሰዎች ኲራት ይጠፋል፤ እብሪት የሞላበት ትዕቢታቸውም ያከትማል፤ ጣዖቶች ሁሉ ይደመሰሳሉ፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ብቻ በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
ይህም በሚፈጸምበት ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “እነሆ፥ እርሱ አምላካችን ነው፤ በእርሱ ስለ ታመንን አድኖናል፤ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ እኛም በእርሱ ታምነናል፤ እርሱ ስለ ታደገን በደስታ ተሞልተን ሐሴት እናደርጋለን!” ይላሉ።
የመሠረቱ መለኪያ ፍትሕ፥ ቱምቢውም ታማኝነት ይሆናሉ፤” መጠጊያችን ነው ብላችሁ የምትተማመኑበትን ሐሰት የበረዶ ወጀብ ይመታዋል፤ የምትሸሸጉበትንም ቦታ ጐርፍ ይጠራርገዋል።
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለረጅም ጊዜ ታገሥኩ፤ ጸጥ ብዬም ራሴን ገታሁ፤ አሁን ግን ምጥ እንደ ያዛት ሴት ከፍተኛ ድምፅ አሰማለሁ፤ የቊጣ እስትንፋስ እተነፍሳለሁ።
“ዕውሮችን ሄደውበት በማያውቁት መንገድ እመራቸዋለሁ፤ ቀድሞ ባላወቁትም መንገድ እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸው የተጋረደውንም ጨለማ ወደ ብርሃንነት እለውጣለሁ፤ ወጣገባ የሆነውንም ስፍራ አስተካክላለሁ፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እኔ የምፈጽማቸው ናቸው፤ አልተዋቸውምም።
እኔ እግዚአብሔር ፍትሕን እወዳለሁ፤ ቅሚያንና ክፉ ድርጊትን እጠላለሁ፤ እኔ ተገቢ ዋጋቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ።
ከጥንት ጀምሮ ተስፋቸውን በእርሱ አድርገው ለሚተማመኑበት ወገኖች እነዚያን ሁሉ ድንቅ ነገሮች ያደረገ አምላክ ከአንተ በቀር አልተሰማም፤ አልታየም፤ የተረዳም የለም።
ለይሁዳ ሕዝቦች ግን ፍቅር አሳያቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ፤ የማድናቸውም በጦርነት ኀይል አይደለም፤ በሰይፍ፥ በቀስትና በፍላጻ ወይም በፈረስና በፈረሰኛ አይደለም።”
በቃላችሁ እግዚአብሔርን አሰልችታችሁታል፤ “እርሱን ያሰለቸነው በምንድን ነው?” ትላላችሁ፤ እርሱን ያሰለቻችሁት፦ “ክፉ አድራጊ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፤ እግዚአብሔርንም ያስደስተዋል” በማለት ወይም “የፍትሕ አምላክ የት አለ?” ብላችሁ በመጠየቅ ነው።
በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ሕይወቱን ለእግዚአብሔር የሰጠ ጻድቅ ሰው ነበር፤ የእስራኤልን የመዳን ተስፋ ይጠባበቅ ነበር፤ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበር።
“እርሱ ምሽጋችን ነው፤ ሥራዎቹም ፍጹሞች ናቸው፤ መንገዶቹም ሁሉ የቀኑ ናቸው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፥ እርሱም ቀጥተኛና እውነተኛ ነው።
ደግሞም እነዚያን በትዕግሥት የጸኑትን “የተባረኩ ናቸው” እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንዴት እንደ ታገሠ ሰምታችኋል። ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን መልካም ነገር አይታችኋል፤ በዚህም ጌታ መሐሪና ርኅሩኅ መሆኑን ተመልክታችኋል።
አንዳንድ ሰዎች እንደሚመስላቸው ጌታ የተናገረውን የተስፋ ቃል ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃና ማንም ሰው እንዳይጠፋ ፈልጎ ስለ እናንተ ይታገሣል።
እስቲ በመታበይ አትጓደዱ፤ የትምክሕት ንግግራችሁንም አስወግዱ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሁሉን ያውቃል፤ ሕዝብ የሚሠራውንም ሁሉ በፍርድ ይመዝናል።