የሰደብከውና የተዳፈርከው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው በማን ላይ ነው? በትዕቢትስ ዐይንህን ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ ነው።
ኢሳይያስ 30:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመንገዳችን ወዲያ ዘወር በሉልን፤ ለእርምጃችንም መሰናክል አትሁኑብን፤ እኛ ስለ እስራኤል ቅዱስ ዳግመኛ መስማት አንፈልግም።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ መንገድ ፈቀቅ በሉ፤ ከጐዳናውም ራቁ፤ ከእስራኤል ቅዱስ ጋራ ፊት ለፊት አታጋጥሙን!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመንገድ ፈቀቅ በሉ፥ ከጐዳናውም ዘወር በሉ፥ የእስራኤልንም ቅዱስ ከእኛ ዘንድ አስወግዱ” ይሏቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከዚህ መንገድ መልሱን፤ ከዚህም ፈቀቅ አድርጉን በሉ፤ የእስራኤልንም ቅዱስ ትምህርት ከእኛ ዘንድ አስወግዱ” ይሏቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመንገድ ፈቀቅ በሉ፥ ከጐዳናውም ዘወር በሉ፥ የእስራኤልንም ቅዱስ ከእኛ ዘንድ አስወግዱ ይሉአቸዋል። |
የሰደብከውና የተዳፈርከው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው በማን ላይ ነው? በትዕቢትስ ዐይንህን ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ ነው።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።
ሰውን በነገር ወንጀለኛ የሚያደርጉ፥ ተከሳሽንም በፍርድ ሸንጎ የሚያጠምዱ፥ በሐሰተኛ ምስክር ንጹሕ ሰው ፍትሕ እንዳያገኝ በሐሰት የሚመሰክሩትን ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል።
የሰውን ስም የሚያጠፉ፥ እግዚአብሔርን የሚጠሉ፥ ሰውን የሚያዋርዱ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክሕተኞች፥ ክፋትን ለማድረግ ዘዴ የሚፈልጉ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥