“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!
ኢሳይያስ 28:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ሕዝብ ላይ ተሾማችሁ ኢየሩሳሌምን የምትገዙ እናንተ ፌዘኞች፥ እግዚአብሔር የሚለውን አድምጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለውን ሕዝብ የምትገዙ፣ እናንተ ፌዘኞች የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለውን ሕዝብ የምትገዙ ፌዘኞች ሆይ፥ የጌታን ቃል ስሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ የተጨነቃችሁ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ያለውን ሕዝብ የምትገዙ አለቆች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለውን ሕዝብ የምትገዙ ፌዘኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። |
“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!
መሪዎችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ግብረ አበሮች ሆኑ፤ እያንዳንዱ ሁልጊዜ ገጸ በረከትና ጉቦ ይቀበላል፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት አይጠብቁም፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ አይሰሙም።
ገንዘብ አበዳሪዎች ሕዝቤን ያራቊታሉ፤ አራጣ አበዳሪዎችም ይበዘብዙአቸዋል፤ ሕዝቤ ሆይ፥ መሪዎቻችሁ ያስቱአችኋል፤ የምትሄዱበትንም መንገድ ያጣምማሉ።
እነሆ የሠራዊት አምላክ እንዲህ ብሎ በመሐላ ሲያረጋግጥ ሰምቼአለሁ፦ “የተዋቡ ታላላቅ ቤቶች ሁሉ ፈርሰው ወና ይሆናሉ፤ የሚኖርባቸው ሰውም አይገኝም።
ይሁዲም ሦስት ወይም አራት ዐምድ ያኽል አንብቦ በጨረሰ ቊጥር ንጉሡ የተነበበለትን ብራና በመቊረጫ ቈራርጦ እሳት ውስጥ ይጥለው ነበር፤ በዚህም ዐይነት የብራናውን ጥቅል በሙሉ አቃጠለው።