በዚህ ጊዜ አሳ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፥ ኀያላኑንም ሠራዊት ሆነ ደካማውንም የመርዳት ችሎታ አለህ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ በአንተ ስለ ተማመንን እነሆ፥ ይህን ብዙ ሠራዊት ለመውጋት መጥተናልና እባክህ እርዳን፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ አምላካችን ነህ፤ አንተን ማሸነፍ የሚችል ማንም የለም።”
ኢሳይያስ 28:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕረፍትንና መጽናናትን ሰጥቶአችሁ ነበር፤ እናንተ ግን እርሱን ማዳመጥ እምቢ አላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ፣ “ይህች የዕረፍት ቦታ ናት፤ የደከመውን አሳርፉ፤ ይህች የእፎይታ ቦታ ናት” ያለው ለማን ነበር? እነርሱ ግን መስማት አልፈለጉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “ዕረፍት ይህች ናት፥ የደከመውን አሳርፉ፤ ይህችም ማረፊያ ናት” አላቸው፤ እነርሱ ግን መስማትን እንቢ አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ይህችም ለደከመ ዕረፍት ናት፤ ይህችም መቅሠፍት ናት፤” አላቸው፤ እነርሱ ግን መስማትን እንቢ አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ዕረፍት ይህች ናት፥ የደከመውን አሳርፉ፥ ይህችም ማረፊያ ናት አላቸው፥ እነርሱ ግን መስማትን እንቢ አሉ። |
በዚህ ጊዜ አሳ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፥ ኀያላኑንም ሠራዊት ሆነ ደካማውንም የመርዳት ችሎታ አለህ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ በአንተ ስለ ተማመንን እነሆ፥ ይህን ብዙ ሠራዊት ለመውጋት መጥተናልና እባክህ እርዳን፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ አምላካችን ነህ፤ አንተን ማሸነፍ የሚችል ማንም የለም።”
የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በመመለስና በማረፍ ደኅንነትን ታገኛላችሁ፤ ጸጥ በማለትና በመታመን ኀይል ታገኛላችሁ፤ እናንተ ግን እምቢ አላችሁ።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “በየጐዳናው ቆማችሁ ተመልከቱ፤ ጥንታዊና መልካም የሆነችው መንገድ የትኛዋ እንደ ሆነች ጠይቃችሁ ተረዱ፤ ባገኛችኋትም ጊዜ በእርስዋ ሂዱ፤ በሰላምም ትኖራላችሁ።” ሕዝቡ ግን “በእርስዋ አንሄድም!” አሉ።
እንደ ዐውሎ ነፋስ ጠራርጌ በመውሰድም በማያውቁት ባዕድ አገር እንዲኖሩ አደረግኋቸው፤ ይህችም መልካም ምድር ማንም የማይኖርባት ባድማ ሆና ቀረች፥ ያቺ ያማረች ምድርም ባድማ ሆነች።”
ያንን የሚናገረውን አንቀበልም እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ እግዚአብሔር በሰው አማካይነት ከምድር ሲናገራቸው አንሰማም ያሉት ካላመለጡ፥ ታዲያ እኛ ከሰማይ የሚናገረንን ባንቀበል እንዴት እናመልጣለን!