ኢሳይያስ 23:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በባሕር ጠረፍ የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ! በዋይታ እያለቀሳችሁ ወደ ተርሴስ ተሻገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በደሴቲቱ የምትኖሩ፣ በዋይታ አልቅሱ፤ ወደ ተርሴስም ተሻገሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ተርሴስም ተሻገሩ፤ እናንተ በደሴት የምትኖሩ አልቅሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ኬልቄዶን ተሻገሩ፤ እናንተ በደሴት የምትኖሩ፥ አልቅሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ተርሴስ ተሻገሩ፥ እናንተ በደሴት የምትኖሩ አልቅሱ። |
“አንቺ የሲዶን ከተማ ሆይ! የደስታሽ ዘመን አክትሞአል፤ ሕዝብሽ ተጨቊነዋል፤ ወደ ቆጵሮስ ሸሽተው ቢያመልጡ እንኳ እዚያ በሰላም አይኖሩም” ብሎአል።
ምስሎቻቸው ከተርሴስ በመጣ ጥሬ ብርና ከኡፋዝ በተገኘ ወርቅ ተለብጠዋል፤ በብልኀተኞችም ሥራ አጊጠዋል፤ ጥበበኞች ሸማኔዎች በሠሩአቸውም የወይን ጠጅና ሐምራዊ ልብስ ተሸፍነዋል።
“በባሕር ጠረፍ የሚኖሩ ሁሉ አንቺን ከገጠመሽ መጥፎ ዕድል የተነሣ ደንግጠዋል፤ ንጉሦቻቸውም እንኳ ሳይቀሩ ተሸብረዋል፤ በያንዳንዳቸውም ፊት ላይ ፍርሀት ይነበባል።
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ለመኰብለል አስቦ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወርዶ ከዚያ ወደ ተርሴስ የምትጓዝ መርከብ አገኘ፤ ለጒዞ የሚያስፈልገውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ ወደ መርከቢቱ ገባ፤ ሐሳቡም ከእግዚአብሔር ለመሸሽ ነበር።