የግብጽ ሕዝብ በፍርሃት እንደ ሴት የሚሆኑበት ጊዜ ይመጣል፤ የሠራዊት አምላክ እነርሱን ለመቅጣት ኀይሉን በሚያሳይበት ጊዜ በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ፤
ኢሳይያስ 23:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጢሮስ መደምሰስዋን በሰሙ ጊዜ ግብጻውያን በድንጋጤ ይታወካሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጢሮስ የሚመጣው ዜና፣ በግብጽ በሚሰማበት ጊዜ ጭንቅ ይይዛቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጢሮስ የሚመጣው ዜና፤ በግብጽ በሚሰማበት ጊዜ ጭንቅ ይይዛቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወሬዋ ወደ ግብፅ በደረሰ ጊዜ ስለ ጢሮስ ምጥ ይይዛቸዋል። |
የግብጽ ሕዝብ በፍርሃት እንደ ሴት የሚሆኑበት ጊዜ ይመጣል፤ የሠራዊት አምላክ እነርሱን ለመቅጣት ኀይሉን በሚያሳይበት ጊዜ በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ፤
ፍልስጥኤም የምትጠፋበት ጊዜ ደርሶአል፤ ከሞት ተርፈው ጢሮስንና ሲዶናን የሚረዱት ሁሉ ተቈራርጠው የሚቀሩበት ጊዜ ተቃርቦአል። እኔ እግዚአብሔር፥ ከሞት ተርፈው በባሕር ዳርቻ የምትገኘው የካፍቶር ዘሮች የሆኑትን ፍልስጥኤማውያን በሙሉ እደመስሳለሁ።
እነሆ ጠፋህ! ለዘለዓለምም አትገኝም፤ ያውቁህ የነበሩ አገሮች ሁሉ ተሸብረዋል፤ በአንተ ላይ የደረሰው መጥፎ ዕድል እንዳይገጥማቸውም ፈርተዋል።’ ”
በዚያን ቀን ‘አንዳች ነገር ይደርስብናል’ ብለው ያልተጠራጠሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራራት መልእክተኞች በእኔ ትእዛዝ ይወጣሉ፤ እነርሱም በግብጽ ላይ በእርግጥ በሚመጣው ጥፋት ምክንያት ይጨነቃሉ።”